“ኅብረተሰቡ በግብይት ወቅት በሀሰተኛ የብር ኖት እንዳይታለል ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል” አቶ ዓለሙ እንዳለው የዓባይ ባንክ ሽምብጥ ቅርንጫፍ ጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅ

99
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 28/2013 ዓ.ም (አብመድ) በባሕር ዳር ከተማ በሚገኙ አንዳንድ የገበያ ሥፍራዎች እየተከናወኑ የሚገኙ ግብይቶችን ባልደረባችን ብሩክ ተሾመ ተዘዋውሮ ቃኝቷል።
አቶ ፋሲል ታደሠ በባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ ናቸው፤ የሚተዳደሩት ደግሞ በንግድ ሥራ ነው። በተለይ ባለ 100 እና ባለ 200 የብር ኖቶችን በጥንቃቄ እንደሚቀበሉ ነው የነገሩን። ለደንበኞቻቸዉ መልስ በሚሰጡበት ወቀት ደንበኞቻቸው ብዙም እንደማያስተውሉ እና ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ወይዘሮ መሠረት ክንዴ ደግሞ እሳቸዉን ጨምሮ በኅብረተሰቡ ውስጥ የጥንቃቄ ጉድለት እንደሚስተዋል ነው የተናገሩት። የሀገር ምጣኔ ሀብት እንዳይዳከምና ማኅበረሰቡም ለኪሳራ እንዳይጋለጥ በቀጣይ ጥንቃቄ እንደማይለያቸው ገልፀዋል።
“ኅብረተሰቡ በግብይት ወቅት በሀሰተኛ የብር ኖት እንዳይታለል ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል” ያሉት ደግሞ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ዓባይ ባንክ ሽምብጥ ቅርንጫፍ ጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለሙ እንዳለው ናቸው፡፡
ኅብረተሰቡ በሃሰተኛ የብር ኖት ኪሳራ እንዳይደረስበት በብር ኖት ላይ የሚገኙ ምልክቶችን ማስተዋል ይገባዋል ብለዋል፡፡ ሀሰተኛ የብር ኖትን ብቻ ሳይሆን የተቀደደና የተፃፈበትንም ጨምሮ መቀበል እንደሌለበት አቶ ዓለሙ አሳስበዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የልደት በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
Next articleየብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተመሥገን ጥሩነህ የልደት በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡