ሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ የዜግነትና የሰላም እሴቶችን ያካተተ ስርዓተ-ትምህርት ለማዘጋጀት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

410
ሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ የዜግነትና የሰላም እሴቶችን ያካተተ ስርዓተ-ትምህርት ለማዘጋጀት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 27/2013 ዓ.ም (አብመድ) በሥነምግባር የታነፀ ዜጋ ለመፍጠር ሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ የዜግነትና የሰላም እሴቶችን ያካተተ ሥርዓተ-ትምህርት ለማዘጋጀት ትምህርት ሚኒስቴር አውደ ጥናት እያካሄደ ነው።
አውደ ጥናቱ በስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ የሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ ዜግነትና የሰላም እሴቶች ላይ ግብዓት መሰብሰብ ዓላማ ያደረገ ነው።
የሚሻሻለው የግብረ-ገብና ዜግነት ትምህርት ከ1ኛ -6ኛ ክፍል የግብረ-ገብ ትምህርት እንዲሁም ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ ደግሞ የዜግነት ትምህርት ተብሎ የሚዘጋጅ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመልክቷል፡፡
ለሚዘጋጀው የግብረ-ገብና ዜግነት ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ከወሎ ዩኒቨርስቲ፣ ከአዲስ ኪነ-ጥበባት የባህል ማዕከል፣ ከኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች፣ የፍልስፍናና የሀይማኖት ሰዎች ጥናታዊ ፅሁፎችን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመድረኩም ከክልል ትምህርት ቢሮ ፣ ከመምህራን ማህበር፣ ከመምህራን ኮሌጆች፣ ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣ ከሴቶችና ህጻናት ሚኒስቴርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡
ከሥርዓተ ትምህርቱ ችግሮች መካከል የግብረ-ገብ ትምህርትን በሚፈለገው ልክ አካቶ አለመያዙ መሰረታዊ ችግር ሆኖ በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው ላይ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ32ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን እጩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ዛሬ እያስመረቀ ነው።
Next article“የባሕር ዳር ከተማ አዲስ መዋቅራዊ ፕላን የከተማዋ እድገት ቀጣይነት እንዲኖረው ፋይዳው የጎላ ነው ” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)