በዜጎች ጭፍጨፋ የሌላ አካል እጂ እንደነበረበት በመተከል ዞን በግድያው የተሳተፉና በቁጥጥር ስር የዋሉ ታጣቂዎች ተናገሩ፡፡

741
በዜጎች ጭፍጨፋ የሌላ አካል እጂ እንደነበረበት በመተከል ዞን በግድያው የተሳተፉና በቁጥጥር ስር የዋሉ ታጣቂዎች ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 25/2013 ዓ.ም (አብመድ) በዜጎች ጭፍጨፋ የሌላ አካል እጂ እንደነበረበት በመተከል ዞን በግድያው የተሳተፉና በቁጥጥር ስር የዋሉ ታጣቂዎች ተናግረዋል፡፡ በሌላ አካል ጫና እና ማስፈራሪያ ተገደው ለግድያ መሰለፋቸውን በመተከል ዞን ዜጎችን በመግደል ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ታጣቂዎች ገልጸዋል፡፡
ከሰሞኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ቡለንና በቆጂ ወረዳዎች ታጣቂዎች በዜጎች ላይ አሰቃቂ ግድያ መፈፀማቸው ይታወሳል።
ከታጣቂዎቹ መካከል በትናንትናው እለት 17ቱ በህዝቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት ሽፍቶች መካከል እንዳሉት ለዚህ እኩይ አላማ የተሰለፉት በሌሎች አካላት ጫና እና አስገዳጅነት መሆኑን ተናግረዋል።
“በግዳጅ በድብደባና እንገድላችኋላን” ተብለን ለመታጠቅ ተገደናል ብለዋል። ለጥፋት የመለመሏቸው አካላት የሚነግሯቸውን ሁሉ እንዲፈፅሙ ትእዛዝ እንደሰጧቸው ተናግረዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጸረ ሽምቅና ልዩ ጥበቃ አድማ ብተና መምሪያ ዋና አዛዥ ኮማንደር ዶሳ ጎሹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ታጣቂዎች ዜጎችን ሲገድሉ ከነበሩት መካከል መሆናቸው ተረጋግጦ ነው ብለዋል።
እነዚህ የታጠቁ ሽፍቶች ከዞኑ ከዳንጉር፣ ከድባጤ፣ ከቡለንና ከማንዱራ ዙሪያ የመጡ መሆናቸውንም ነው የሚናገሩት።
ኢዜአ እንደዘገበው በአካባቢው ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል የጸጥታና ህግ የማስከበር ስራውን ተረክቦ የተጠናከረ ርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኮማንደሩ ተናግረዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article‹‹መቻሬ ወልዲያ ሳንቃ ደሮ ግብር፣ ያመዋል ሲነካ የራያ ልጅ ክብር፣ አትንኩት ራያን ድርድር አይወድም፣ ክብሩን በድርድር አሳልፎ አይሰጥም››
Next articleበአርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ የሚመራው የዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት አንድ ሚሊዮን ብር ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ።