“ትህነግ የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክትን ይዞ መነሳቱ ሀገርን ለከፋ ችግር ጥሎ አልፏል” የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብርሃም አለኸኝ

417
“ትህነግ የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክትን ይዞ መነሳቱ ሀገርን ለከፋ ችግር ጥሎ አልፏል” የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብርሃም አለኸኝ
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 25/2013 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የወጣቶች ሚና እና ዓለም አቀፋዊ ልምዶች በሚል ርዕሰ ጉዳይ ምክንያታዊ ወጣት መፍጠርን ዓላማ ያደረገ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል::
በመድረኩም በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ወጣቶች ተሳተትፈዋል::
የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብርሃም አለኸኝ ለወጣቶች ባስተላለፉት መልዕክት በሀገረ መንግሥት ግንባታ በተካሄዱ የለውጥ ሂደቶች የወጣቶች ሚና ከፍተኛ እንደነበር አንስተዋል::
አቶ አብርሃም እንዳሉት ወጣቶች የደም ዋጋ የከፈሉላቸው ሀገራዊ ለውጦች ሀገርን በማይወዱ መሪዎች ምክንያት ዓላማቸው ሳይሳካ ቀርቷል:: ትህነግ የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክትን ይዞ መነሳቱ ሀገርን ለከፋ ችግር ጥሎ ማለፉንም አቶ አብርሃም ተናግረዋለ፡፡
በዜጎች መካከልም መጠራጠርንና አለመተማመንን ፈጥሯል፤ በተለይም የአማራ ሕዝብ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ በጠላትነት እንዲፈረጅ በተሠራው የሃሰት ትርክት ምክንያት ዜጎች ተወልደው ባደጉበት ቀየ በማንነት እንዲገደሉና እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል ብለዋል አቶ አብርሃም::
አቶ አብርሃም ሁሉም ነገር ከሰው በታች ቢሆንም አሁን ላይ በተዘራው መጥፎ ዘር ምክንያት ዜጎች በተኙበት የሚገደሉበት ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ ፖለቲካም እምነትም ከሰው ልጆች በታች ነውና እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ይገባል ብለዋል::
ሀገርና ትውልድ በአንድና ሀለት ትውልድ አይቆምም ያሉት የአማራ ብልጽግና ወጣቶች ሊግ ኀላፊ አቶ ጋሻው ተቀባ ሀገርን ከነ ሙሉ ክብሩ የማስቀጠል ኀለፊነት በዚህ ትውልድ ላይ የተጣለ እንደሆነ አንስተዋል::
በሀገራዊ የለውጥ ሂደቱ የአማራ ወጣቶች ከሌሎች ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን ትልቅ መስዋእትነትን ከመክፈል ጀምሮ አሁን ላይ በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ላይ የተወሰደውን ሕግ የማስከበር ርምጃ ደሙን በመለገስ፣ በገንዘቡና በጉልበቱ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡ ወጣቶች ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል::
በየአካባቢው በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ በማስቆም ዜጎች በተወለዱበት፣ ባደጉበትና ሀብት በፈጠሩበት ቀየ ተረጋግተው እንዲኖሩ በየአካባቢው ያሉ የአስተዳደር አካላትና የፌደራል መንግሥት ኀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አቶ ጋሻው ጠይቀዋል::
ዘጋቢ፡- ዘላለም አስፋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል፤ 500 ሺህ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል” ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ
Next article‹‹መቻሬ ወልዲያ ሳንቃ ደሮ ግብር፣ ያመዋል ሲነካ የራያ ልጅ ክብር፣ አትንኩት ራያን ድርድር አይወድም፣ ክብሩን በድርድር አሳልፎ አይሰጥም››