“የትምህርት ሴክተሩ ከሙስና የፀዳ እንዲሆን እየተሠራ ይገኛል” ትምህርት ሚኒስቴር

163
“የትምህርት ሴክተሩ ከሙስና የፀዳ እንዲሆን እየተሠራ ይገኛል” ትምህርት ሚኒስቴር
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) የትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ 16ኛውን የፀረ ሙስና ቀንን አስመልክቶ ባዘጋጀው በድረክ የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶክተር) በትምህርት ሴክተሩ ላይ የሙስና ሥራዎችን በመከላከል እና በማስቀረት በሥነምግባር የታነፀ ትውልድ ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
በትምህርት ሥርዓቱም ግብረ ገብነት እንዲተገበር ትምህርት ሚኒስቴር እየሰራ እንደሆነም ተገልጿል።
ሙስና ከገንዘብ ጋር ብቻ የተገናኘ ሳይሆን ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም በራሱ ሙስና ነው ያሉት ሚነስትሩ ለጊዜ ዋጋ በመስጠት ሀገራችን የጣለችብንን ሃላፊነት ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ በፀረ ሙስና እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ተሳታፊዎች ውይይት አድርገውበታል።
ቀኑ “የትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፒሊን በመምራት ሌብነትና ብልሹ አሥራርን በመታገል የብልፅግና ጉዟችንን እናፋጥናለን” በሚል መሪ መልዕክት ነው ተከብሮ የዋለው።
የዘንድሮው የፀረ ሙስና ቀን በሀገራችን ለ16ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል። መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየጥምቀት በዓል በጎንደር ከተማ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ዝግጂት እየተደረገ ነው፡፡
Next articleየሀውጃኖ እውነት ቆይቶውም ቢሆን ተገልጧል።