
የጥምቀት በዓል በጎንደር ከተማ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ዝግጂት እየተደረገ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓልን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እና የጸጥታ አካላት በጋራ እየሠሩ ነው፡፡
በዚህ ዓመት የሚከበረው የጥምቀት በዓል በሰላማዊና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጎንደር ከተማ የሠላምና ሕዝብ ደኀንነት መምሪያ አስታውቋል፡፡
የበዓሉን አከባበር በተመለከተ የከተማዋ ነዋሪዎችና የጸጥታ አካላት ባካሄዱት የምክክር መድረም በየደረጃው እቅድ ተዘጋጅቶ እየተሰራ እንደሆነ ተብራርቷል፡፡
በጥምቀት በዓል የሚታደመው እንግዳ ጥሩ ትዝታ ይዞ እንዲሄድ የጸጥታ አካላት እና ማሕበረሰቡ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የሠላምና ሕዝብ ደኀንነት መምሪያ ኀላፊ አቶ ናትናኤል ጎሹ የጥምቀት በዓል በሠላም እንዲከበር ለማድረግ ጊዜውን የዋጀ የደኅንት ሥራ ከመቸውም ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ሁሉም የጸጥታ አካል በዓሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ልዩ ተልኮ እንደተሰጠውም ገልጸዋል፡፡ ሕብረተሰቡ እና የጸጥታ አካላት ተባብረው የሚሰሩበት ሁኔታ መፈጠሩንም ጠቁመዋል፡፡
በከተማዋ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የበዓሉ እንግዶች ያለስጋት ነጻ ሆነው እንዲያከብሩ የሚያስችል ቅድመዝግጅት መደረጉንም አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ምስጋናው ብርሃኔ- ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ