
በባሕርዳር የባህል ሙዚቃ፣ የታንኳና ስፖርት ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) ጥርን በባሕርዳር የተሰኘ የባህል ሙዚቃ፣ ታንኳና የስፖርት ፌስቲቫልን ያካተተ ዝግጅት በባሕር ዳር ሊካሄድ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታውቋል፡፡
የመምሪያው ኀላፊ አቶ አብረሃም አሰፋ እንደተናገሩት የባሕርዳር ከተማ ትልቅ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸዉ የሀገር ዉስጥና የዉጪ ሀገር ጎብኝዎች በየዓመቱ ይመጣሉ፤ በመሆኑም በጥር የሚካሄደዉ ሁነት የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ሁነት የታንኳ ቀዘፋ፣የጀልባ ትርኢት የሚካሄዱ ሲሆን ይህ ዝግጅት የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ከተማዋ ከቱሪዝም ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
የታንኳ ቀዛፊዎች፣የግልና የድርጅት የጀልባ ባለንብረቶች አስፈላጊዉን የቅድመ ዝግጅት ሥራ እንዲያጠናቅቁና ሌሌች የግልና የመንግሥት ተቋማት እንዲሁም የከተማዋ ማሕበረሰብ የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ የመምሪያዉ ኀላፊ አስገንዝበዋል፡፡
በ2010 ዓ.ም መከበር የጀመረው ፌስቲቫሉ ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄድ ነው፡፡ ከጥር 10 እስከ 30/2013 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መሆኑንም የከተማ አስተዳደሩ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ