
በ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የተገነባው የቦርት ማልት ብቅል ፋብሪካ በደብረ ብርሃን ከተማ ሥራ ጀመረ።
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በሰሜን ሸዋ ዞን ያሉ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ የሚነሱ ችግሮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ ላይ ወደ ሥራ የገቡ ሁለት ኢንዱስትሪዎች ተጎብኝተዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኩ ወደ ሥራ የገባው ኢኬ የተሰኘ ሹራብ አምራች ኩባንያ ምርቶቹን ወደ ውጪ በመላክ የውጪ ምንዛሬ እያስገኘ እንደሆነ ተገልጿል።
በሀገሪቱ ያሉ የቢራ ፋብሪካዎችን የብቅል ፍላጎት የሚያሟላ በ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የተገነባው የቦርት ማልት ብቅል ፋብሪካም ስራ ጀምሯል።
በደብረ ብርሀን ከተማ ተገንብተው ወደ ሥራ የገቡ ኢንዱስትሪዎች በሥራ እድል ፈጠራና በኢኮኖሚው ዘርፍ እያስገኙት ያለው እድል አበረታች መሆኑ ተመላክቷል።
ዘጋቢ፡- ኤሊያስ ፈጠነ- ከደብረ ብረሃን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ