
“ኢትዮጵያ የባህላዊ ማዕድን አውጪዎችን እና የማኀበረሰቡን ሕይወት ለማሻሻል የሚያስችሉ የተፈጥሮ ማዕድናትን የያዘች ሀገር ናት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 21/2013 ዓ.ም (አብመድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶክተር) ኢትዮጵያ እሴቶችን በመጨመር በየአካባቢው የሚገኙ ባህላዊ ማዕድን አውጪዎችን እና የማኀበረሰቡን ሕይወት ለማሻሻል የሚያስችሉ፣ በርካታ የተፈጥሮ ማዕድናትን የያዘች ሀገር ናት ብለዋል።
ወርቅ፣ ቤዝ ብረቶች፣ ፖታሽ፣ ታንታሉም፣ ሰንፔር፣ ኤመራልድ እና ኦፓል ከታደልናቸው ማዕድናት ወስጥ ጥቂቶቹ ናቸውም ብለዋል።
ለማምረት የሚያስችለንን ሀገራዊ ዐቅም በመፍጠር፣ የውጪ ገበያ እና የውጪ ምንዛሬ የማግኘት ዐቅማችንን ማጠናከር አለብን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ