በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡ ስምንት ትምህርት ቤቶች ለርክክብ ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ።

457
በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡ ስምንት ትምህርት ቤቶች ለርክክብ ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ታኅሥሥ 21/2013 ዓ.ም (አብመድ) በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በመገንባት ላይ የሚገኙ ግንባታቸው ከዚህ ቀደም ተጠናቆ ለአገልግሎት ከበቁ ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታወቀ።
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፋንታው እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጠናቀው ስራ ከጀመሩት በተጨማሪ የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።
ግንባታቸው ተጠናቆ ርክክብ የሚፈጸምባቸው ትምህርት ቤቶች በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ እና ሳህላ ሰለምት ወረዳ፣ በአፋር ክልል ዱብቲ፣ በጋምቤላ አኝዋክ ዞን፣ በቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ እና መተከል ዞን ፣ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ዞን እንዲሁም በዲላ ከተማ 02 እና 06 ቀበሌዎች የተገነቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ግንባታቸው ቀድመው የተጠናቀቁና ርክክባቸው ተፈጽሞ ሥራ የጀመሩት አምስት ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፤ በአማራ ክልል ጎንደር ሎዛ ቀበሌ፣ ደቡብ ወሎ ጦሳ ሰላማ ቀበሌ (አልብኮ ወረዳ)፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሊበን ጭቋላ ቀበሌ (ቢሾፍቱ አካባቢ)፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን እና በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ውጫሌ ወረዳ ጃክ ቀበሌ (ሙከጡሪ አካባቢ) የሚገኙት መሆናቸውንና አሁን ላይ ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል።
ግንባታቸው እስከ ታኅሣሥ 30/2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁ አራት ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ ትምህርት ቤቶቹም በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሸካ ዞን፣ ጌዲኦ ዞን፣ ደቡብ ኦሞ እና በኦሮሚያ ክልል ሐዊ ጉዲና ወረዳ ሐሮ ቢሊቃ ቀበሌም እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
በአዲስ አበባ የተሰራው የሕጻናት ማሳደጊያ፣ በሰበታ ከተማ የሚገኘውን አይነስውራን ትምህርት ቤት እና በተለያዩ ክልሎች የተገነቡትን ክፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገንብቶ ለማጠናቀቅ ጽኅፈት ቤቱ እስካሁን 760 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታውቀዋል። ገንዘቡም ከተለያዩ የውጭ ሃገራት ረጂ ድርጅቶች የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህ ዓመትም 10 ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ተይዞ የአምስቱ የግንባታ ቦታ መለየቱን የጠቀሱት አቶ ሙሉቀን፤ የእነዚህ ፕሮጀክቶች ወጪ የሚሸፈነውም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ.ር) ከመደመር መጽሐፍ ሽያጭ ያገኙትንና ለጽሕፈት ቤቱ ባበረከቱት ገንዘብ መሆኑን መግለፃቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“በትግራይ ክልል በነበረው ሕግ የማስከበር ተግባር ሴቶች ቆራጥነታቸውንና ጀግንነታቸውን በተግበር አሳተዋል” የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወርቅሰሙ ማሞ
Next articleለግብርና ምርቶች ጥራት ትኩረት መስጠታቸው ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው የምርቱ አቅራቢ ነጋዴዎች ተናገሩ፡፡