
እየሩሣሌም የህፃናትና ማኅበረሰብ ልማት ድርጅት በዘጌ አካባቢ በትምህርት፣በውኃና በኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች ያከናወናቸውን ሥራዎች ርክክብ ሊያካሂድ ነው።
ባሕር ዳር፡ ታኅሥሥ 20/2013 ዓ.ም (አብመድ) የእየሩሣሌም የህፃናትና ማኅበረሰብ ልማት ድርጅት የባሕር ዳር ሥራ አስኪያጅ አቶ እደግልኝ ፈንታ ድርጅቱ በአካባቢዉ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን አስረድተዋል።
ኅብረተሰቡ በቡና እና በአትክልት ልማት ብሎም በሌሎች ዘርፎች ተጠቃሚ እንዲሆን ድርጅቱ መሥራቱን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
ድርጅቱ በዘጌ አካባቢ(በኡራ፣ ይጋንዳና አፋፍ 01 ቀበሌዎች) በትምህርት፣ በውኃና በኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች ያከናወናቸውን ሥራዎች ርክክብ ሊያካሂድ ነው።
ዘጋቢ፡- ብሩክ ተሾመ – ከዘጌ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከቆይታ በኃላ የምናደርስ ይሆናል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ