ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን የመከላከያ እና የአማራ ልዩ ኃይል አባላትን ጎበኙ፡፡

286
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን የመከላከያ እና የአማራ ልዩ ኃይል አባላትን ጎበኙ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 20/2013 ዓ.ም (አብመድ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው የምዕራብ እዝ መከላከያ ሆስፒታል እና የልዩ ኃይል የቁስለኞች ማቆያ በመገኘት በትግራይ ክልል በተደረገው የሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን የመከላከያ እና የአማራ ልዩ ኃይል አባላትን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ኂሩት ካሣው፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሠራተኛ እና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ሙሉነሽ አበበን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፈዋል።
በሕግ ማስከበር ሀገራዊ ተልዕኮው ወቅት ለደረሰው የአካል ጉዳት ድጋፍ እንዲሆን ለሆስፒታሎቹ የዊልቸር፣ ክራንች እና ዎከር ድጋፍ ተደርጓል።
በተያያዘ ዜና የሀገር ዳር ድምበር በማስከበር ለሀገር ውለታ የዋሉ ጀግኖች ልጆች መኖሪያ የነበረውንና የፈረሰውን የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ሕፃናት አምባ መልሶ ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑ ታውቋል።
የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ሕፃናት አምባ መቋቋም ለሀገር ክብር ዘብ ለቆሙ ጀግኖች እና ወላጆቻቸውን መሥዋዕት ላደረጉ የጀግኖች ልጆች ተገቢውን ቦታ እና ክብር መስጠት እንደሚያስችል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢብኮ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአፍሪካ አህጉር አቋራጭ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነውና በቅርቡ የተመረቀው የኢትዮ- ኬንያ መንገድ የኢትዮጵያን የወደብ አማራጭ የሚያሰፋ መሆኑ ተገለፀ።
Next articleእየሩሣሌም የህፃናትና ማኅበረሰብ ልማት ድርጅት በዘጌ አካባቢ በትምህርት፣በውኃና በኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች ያከናወናቸውን ሥራዎች ርክክብ ሊያካሂድ ነው።