
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 15/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሸን የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ዕድገት ለማሳካትና ለመምራት የሚያስችል ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ያተኮረ ጥናት ረቂቅ ሪፓርት ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።
በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ዘለቄታዊ ልማት የሚመራ ጥናት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ጥናቱ እንደ አገር የመጀመሪያ መሆኑንና ኢትዮጵያ ያላትን ሀብት የመሬት ሁኔታ በማየት የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
አሁን ያሉትን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከመምራት ባለፈ ወደ ፊት የሚመሰረቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ከምስረታቸው ጀምሮ በማገዝና በመምራት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ፣ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስና በየትኛው አካባቢ ምን አይነት ኢንደስትሪ ፓርክ መገንባት አለበት የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማትን በዘላቂነት ለመምራት ይፋ በሆነው ስፓሻል መሪ ዕቅድ ላይ የመድረኩ ተሳታፊዎች እየተወያዩበት እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m