
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትህነግ በከፈተው ጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 14/2013 ዓ.ም (አብመድ) ከተማ አስተዳደሩ ለመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ በሕግ ማስከበር ርምጃው ላሳየው ተሳትፎም አድናቆቱን ገልጿል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰለሞን ፍስሃ 3 ሺህ ኩንታል ጤፍ፣ ስንዴና በቆሎ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በአማራ ክልል ካሁን ቀደም ተመሳሳይ ድጋፍ ከከተማ አስተዳድሩ ማድረጉንም አስታውሰዋል፡፡ በቀጣይም ተደጋግፈን የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል እንሰራለን ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ (ዶክተር) እንደተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ያደረገው ድጋፍ ለሌሎች አርዓያ የሚሆን ነው፤ ለተደረገው ድጋፍም በክልሉ ሕዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ