ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ዓሥር ዓመታት ሦስት ሳተላይቶችን ታመጥቃለች፡፡

482
ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ዓሥር ዓመታት ሦስት ሳተላይቶችን ታመጥቃለች፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሦስት ሳተላይቶችን እንደምታመጥቅ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ እንደገለፁት፤ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ውስጥ ለተለያዩ አግልግሎቶች የሚውሉ ሦስት ሳተላይቶችን ለማምጠቅ ታቅዷል።
በአሥር ዓመቱ ከሚመጥቁት ሳተላይቶች ውስጥ አንደኛው የኮሚዩንኬሽን እና ብሮድካስት ሲሆን፤ የተቀሩት ሁለቱ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ናቸው።
እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ፤ የኮሚዩንኬሽን እና ብሮድካስት ሳተላይት የሚባለው በብሮድካስት ሚዲያዎች ለኢንተርኔት፣ ለስክልና ለኮሚዩንኬሽን አገልግሎት የሚውል ነው። በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን እነዚህን አገልግሎቶች ከውጭ በመከራየት በሚሊዮን ዶላር የሚገመት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ታወጣለች።
ለአብነትም፣ ከብሮድካስቲንግ በዓመት እስከ አሥር ሚሊዮን ዶላር ወጪ ይደረጋል። ለቴሌ ኮሚዩንኬሽን ደግሞ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ወጭ ይሆናሉ። ስለዚህ ሳተላይት የመገንባት እቅዱን በተግባር በማረጋገጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪን መቀነስ ተገቢ ነው።
ዘገባው የኢትዮ ፕረስ ነው::
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየህግ የበላይነት ለሃገራዊ ልማት በሚል ርዕስ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ያሳተሙት መጽሃፍ ተመረቀ።
Next article“በራያ አዲስ ዓመት በዚህ ወር የገባ ይመስላል”