የህግ የበላይነት ለሃገራዊ ልማት በሚል ርዕስ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ያሳተሙት መጽሃፍ ተመረቀ።

735
የህግ የበላይነት ለሃገራዊ ልማት በሚል ርዕስ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ያሳተሙት መጽሃፍ ተመረቀ።
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ሚኒስትሮች ሙህራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በአዲስ አበባ መጽሃፉ ተመርቋል ።
ደራሲው ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በፌዴራል ፖሊስ ኦፊሰርነት ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት የዜጎችን መብት ቀርቶ የራሳቸውን መብት ማስከበር ባለመቻላቸው ስርዓቱን ለመጣል ወደትጥቅ ትግል የገቡ ሲሆን 7 ዓመታትን በዚህ ሁኔታ እንዳሳለፉ ተነግሯል ።
ደራሲው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እና ሁለተኛ የማስተርስ ዲግሪያቸውን በስዊዲን ሀገር የተከታተሉ ሲሆን መጽሐፉ በዋናነት ለመመረቂያቸው የጻፏቸውን ጥናታዊ ጽሑፎች መሰረት በማድረግ ተተርጉሞ የቀረበ ነው።
ምሁራንም ይህ መጽሐፍ በስልጣን ላይ ያሉ አካለት ሳይንስን ከተግባር ጋር አጣጥመው የጻፉት በመሆኑ ለሌሎች የመንግስት የሥራ ኀላፊዎችም ትምህርት የሚሆን ነው ብለዋል።
በተለይ የሕግ የበላይነት አንዲከበር በዘርፉ ያለ ሰው የጻፈው በመሆኑ ሁሉም ለሕግ ተገዥ አንዲሆን ለማድረግ ጥሩ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ እና በተለይም ለዘርፉ አስፈላጊ መጽሐፍ ነው ብለውታል ምሁራኑ።
ደራሲው በቀጣይም ሌሎች መጽሐፍትን መጻፍ አንደሚቀጥሉ የተናገሩ ሲሆን መጽሐፉ መመረቅ ከነበረበት ጊዜ በኮሮናቫይረስ መክንያት ቢዘገይም ወራሪውና አሸባሪው ትህነግ ድል በተመታበት ማግስት መመረቁ አንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
የብሄራዊ መረጃ ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህም ደራሲው ሲታገሉት የነበሩት ሥርዓት ወድቆ መጽሐፉ መመረቁ ትክክለኛ ጊዜ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ለሕግ የበላይነት መከበር ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ መጽሐፍ ነው ያሉት ባለሃብቶችም ለተለያዩ ትምህርት ቤቶችና የመንግሥት ሰራተኞች አንዲያነቡት ለማድረግ የ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የህግ የበላይነት ለሃገራዊ ልማት በሚል የታተመውን መጽሐፍ ገዝተን እናከፋፍላለን በማለት ቃል ገብተዋል።
ዘጋቢ: አንዱአለም መናን ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአማራ ክልል ህዝቦች ሰማህታት መታሰቢያ ሐውልት ጽሕፈት ቤትየክልሉን ባህልና እሴት በጠበቀ መልኩ በአዲስ መልክ እየተደራጀ መሆኑን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ።
Next articleኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ዓሥር ዓመታት ሦስት ሳተላይቶችን ታመጥቃለች፡፡