
የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማህታት መታሰቢያ ሐውልት ጽሕፈት ቤትየክልሉን ባህልና እሴት በጠበቀ መልኩ በአዲስ መልክ እየተደራጀ መሆኑን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማህታት መታሰቢያ ሐውልት ጽሕፈተ ቤት በ2001 ዓ.ም ከደርጅት ወደ መንግስት የተዛወረ የክልሉ መንግስት ተቋም ነው፡፡ ተቋሙ በህዝቡ ዘንድ የእኛነው የሚል አመኔታ አለመኖሩና በህብረተሰቡ ዘንድ የፖለቲካ ተቋም አድርጎ መመልከት አለፍ ብሎም የባለፉት ፖለቲካዊ ስህተቶች ምልክት /Symbol/ አድርጎ ይመለከተዋል፡፡ የሚሻሻሉ ጉዳዮችንም አስተያየት ይሰጣል ግን ፈጣን ምላሽ ባለመሰጠቱ አሁን ያለው መንግስትና ፓርቲ እንዳይሻሻል ፍላጎት እንዳለው አድርጎ ያስባል፡፡
የተቋሙ ስያሜና የውስጥ ይዘቱ አለመጣጣሙን አስተያየት ሰጭዎችና የተቋሙ ሰራተኞች ያምናሉ፡፡
በተቋሙ መልሶ የማደራጀት ጅማሮ ሥራዎች በ2012 እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ከባህርዳር ዩንቨርስቲ ጋር በመነጋገር ለማጥናት ፕሮፖዛል ተዘጋጅቶ የጥናት ገንዘብ ባለመገኘቱ ባለበት ቁሟል፡፡
የክልሉ መንግስትም በዚሁ ዓመት ጉዳዩ ቀርቦ ተጠንቶ ይቅረብ የሚል አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
የማደራጀት ሙከራዎች ጅማሮ ቢኖርም ብዙም ሳይገፋበት ቆይቶ በ2013 በጀት ዓመት የተሟላ የማደራጀት ሥራ ተጀምሯል፡፡
ተቋሙ በወቅቱ ምስጋና የሚገባቸው ደሞዛቸውን እየከፈሉ በከፍተኛ ተሳትፎ የተገነባ፡ ህንፃዎች መጠነኛ ማስተካከያ ከሚፈልጉት ወጭ በጥራት የተገነቡ፣ አባይ ከጣና ሐይቅ መውጫ ላይ ያለና ለመስብነት ስትራቴጅክና የከተማው መሃል የሆነ ቦታ የያዘ ስለሆነ ህዝቡ በሚፈልገው መንገድ ከተስተካከለ ለክልሉ ህዝብ ትልቅ ሀብት ነው፡፡
ከህዝቡ ሥነ ልቦና እና ፍላጎት አኳያ ተቋሙ እንደገና ከነባሩ መሻሻል ያለባቸው ስያሜውን በመለወጥ የማህበረሰቡን እሴቶች ላይ በማተኮር ከፍታ ላይ የደረሰ የታሪክ አሻራ ያለን (ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን፤ጥንታዊ ገዳማት፣ ጎንደር ቤተ-መንግስት፣ አንኮበር ቤተ-መንግስት፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ቤተ-መንግስት፣ ንጉስ ሚካኤል ቤተ-መንግስት ፡ባህርዳር ቤዛዊት ቤተመንግስት) የተፈጥሮ ጸጋ ባለቤት (ጣናሃይቅ፤ አባይወንዝ፤ ፋፋቴዎች፤ ራስ ደጀን ተራራ፤ሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ፤ አልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ)፤ እንዲሁም የባህል፡ማህበራዊና አኮኖሚያዊ ሁነቶች ወዘተ…ባለቤት ነን፡፡
ከየክፍለ ዘመኑ ከትውልድ ተሻጋሪ ሰራዎች መማርና ስነ ልቦናን ለተሻጋሪ ስራ ማዘጋጀት፤ ታታሪነትና ጥበብ (Wisdom) ያለው ማህበረሰብ መገንባት፤ በራስ ማንነት ቋንቋ እና ባህል የሚኮራ ትውልድ መገንባት፤ ለውጭ ወራሪ የማይበገር ማህበረሰብ መፍጠር ድክመቶች ላይ አለማተኮር (የውጭ ሃገራት ወረራ ጥቃት ፤ ጭሰኝነት ፤ ቀይሽብር ፤ ነጭሽብር ፤ ኢፍትሃዊነት፤ ዘር ተኮር ጥቃት) በአዲሱ ምልከታችን ቅኝት ይሆናል፡፡
በአዲስ የሚሰጠው ስያሜ የያዘውን ሃሳብ ለማስረጽ በኪነቅርጽ (የንጉስ ላሊበላ፤ የንጉስ ፋሲለደስ፤ የአፄ ቴወድሮስ፤ አፄ ሚኒሊክ ፤የእትጌ ፀሐይቱ፤ የንጉስ ተክለኃይማኖት፤ የንጉስ ሚካኤል፤ የደጃዝማች በላይ ዘለቀ፤ የአሁኑን የፍትህና ዴሞክራሲ ትግል ወካይ ኪነሀውልት) በሙዚየም ወስጥ አደረጃጀት በመልዕክቶች (ታላቅ ነበርን ታላቅም እንሆናለን!) በንባብ ቤቶች በኢንተርኔት ቴክኖሎጅ በአንፊ ቲያትር በስዕል ጋላሪ በጋርደኖች በልዩ ልዩ መዝናኛ ዘዴዎች የማስረጽ አላማ ይዞ ይደራጃል፡፡
ከስያሜ ለውጡ ቀጥሎ በዋናው በር የተሸናፊነት ምልክት የሚያሳየው መሳሪያ ዘቅዝቆ የተከዘውን ሽማግሌ ኪነ ቅርጽ ማንሳትና በሌላ አሸናፊነትን በሚወክል ኪነ ቅርጽ መተካት እና ከኪነ ቅርጾች የተገለበጠውን ካርታ ማንሳት፤ ሙዚየም ከ1973 እስከ 1983 ብቻ ያተኮረውን ወደ ኃላና ወደ ፊት ያለውን በሶስት የታሪክ ዘመናት (የጥናታዊ ዘመን ታሪክ የመካከለኛው ዘመን ታሪክ የዘመናዊው ዘመን ታሪክ) ማደራጀት የሥዕል ጋላሪውን የተፈጥሮ መስዕብ የታሪክ ሁነት የባህልና የኢኮኖሚ ሁነቶችን ይዞ አካባቢውን በሚገልጽ መንገድ ለማደራጀት እየተሰራ ነው፡፡
ቤተ መጽሐፍቱ የአዋቂዎችና የታዳጊዎች ሆኖ በቴክኖሎጅ ታግዞ እንዲደራጅ እየተሰራ ነው፡፡
ተቋሙ ስትራቴጅክ ቦታ ላይ ስለሆነ ለመዝናኛ ምቹ በመሆኑ ባሉን ክፍት ቦታዎች የከተማውን እድገት የሚመጥን መዝናኛ ቤቶች ባለሃብቱን በማሳተፍ ተገንብተው አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡
በተቋሙ አደረጃጀት የክልሉ ህዝብ ከጎን ሆኖ እንዲደግፍ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ