የአማራ ሴቶች ማህበር በአዲስ አበባ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

519
የአማራ ሴቶች ማህበር በአዲስ አበባ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ሴቶች ማህበር በአዲስ አበባ ሰባተኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡ በጉባኤው የ2012 ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና በ2013 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
ማህበሩ በ2012 ዓ.ም በኮሮናቫይረስ ምክንያት በታሰበው ልክ ተግባሩን ባያከናውንም ለህዳሴው ግድብ ቦንድ መግዛቱ፣ የችግኝ ተከላ ማካሄዱና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ደም መለገሱ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
ማህበሩ በ2013 በጀት ዓመት የአባላቱን ቁጥር ለመጨመርና ማህበሩን ለማጠንከር፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በትብብር ለመፍታትና የማህበሩን ገቢ በአባላቱ መዋጮ ለማሳደግ አቅዷል፡፡ ከአልማ ጋር በመተባበር ትምህርት ቤቶችንና የጤና ተቋማትን በመገባት የክልሉን ልማት ማገዝም የእቅዱ አካል ነው፡፡
ከአባላቱ መዋጮ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ የሻደይ አሸንድየንና ሶለል በዓላትን ከበፊቱ በተለየ መልኩ እንዲከበሩ በማድረግና ሴቶችን በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳታፊ እዲሆኑ ማስቻል የማህበሩ የቀጣይ እቅዶች እደሆኑም በውይይቱ ተጠቅሷል፡፡
ዘጋቢ፡- ራሄል ደምሰው-ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበምስራቅ ጎጃም ዞን የእናርጂና እናውጋ ነዋሪዎች 2 ሚሊን ብር የሚጠጋ ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ ለአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ድጋፍ አደረጉ፡፡
Next articleየብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየዉን መደበኛ ስብሰባ አጠናቀቀ፡፡