በምስራቅ ጎጃም ዞን የእናርጂና እናውጋ ነዋሪዎች 2 ሚሊን ብር የሚጠጋ ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ ለአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ድጋፍ አደረጉ፡፡

222
በምስራቅ ጎጃም ዞን የእናርጂና እናውጋ ነዋሪዎች 2 ሚሊን ብር የሚጠጋ ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ ለአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ድጋፍ አደረጉ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) የደብረወርቅ ከተማ ነዋሪ አቶ ስሙየ ፈንታ ወራሪውን፣ ተስፋፊውንና አሸባሪውን ትህነግ ለሕግ ለማቅረብ ትህነግ መንግሥት እየወሰደ ያለው ርምጃ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ድጋፉ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ትህነግ በሀገራችን በተለይ ደግሞ በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ መፈናቀል፣ ሞትና ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ሲያደርስ መቆየቱን የተቀሱት አቶ ስሙየ የአካባቢው ነዋሪዎች በቁጭት ከመከላከያ ሰራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ጎን በመሰለፍም 5 ቀን ባልሞላ ጊዜ ከፍተኛ ድጋፍ ማሰባሰቡን ተናግረዋል፡፡
የእናርጂና እናውጋ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ታረቀኝ ጀንበሬ ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ የወረዳው ነዋሪዎች ገንዘብ፤ እህልና የእርድ እንሰሳት ድጋፍ በማድረግ ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል ብለዋል፡፡
በሀገራችን አለመረጋጋት እዲፈጠር ሲሰራ የቆየው ወራሪው፣ ተስፋፊውና አሸባሪው የትህነግ ቡድን ለሕግ እስኪቀርብ ድረስ ድጋፉ እደሚቀጥል ኀላፊው ተናግረዋል፡፡
የወረዳው ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አበበ በለጠ በበኩላቸው በወረዳው መምህራን፤ ተማሪዎችና የትምህርት ባለሙያዎች ከ1መቶ ሀምሳ ሺህ ብር በላይ ገንዘብ በማዋጣት ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
የእናርጂና እናውጋ ነዋሪዎች እስከአሁን 2 ሚሊን ብር የሚጠጋ ሃብት በማሰባሰብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ ለአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ሸምስያ በሪሁን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article‹‹ወንጀል ፈጽመው ወደጎረቤት ሀገራት የሸሹ የጁንታው አባላት የሰላም ጠንቅ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ሥራ መሠራት አለበት›› ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ
Next articleየአማራ ሴቶች ማህበር በአዲስ አበባ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡