‹‹ወንጀል ፈጽመው ወደጎረቤት ሀገራት የሸሹ የጁንታው አባላት የሰላም ጠንቅ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ሥራ መሠራት አለበት›› ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ

238
‹‹ወንጀል ፈጽመው ወደጎረቤት ሀገራት የሸሹ የጁንታው አባላት የሰላም ጠንቅ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ሥራ መሠራት አለበት›› ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) በግጭቱ ወቅት ወንጀል የፈፀሙና ሸሽተው ወደጎረቤት ሀገራት የሄዱ ወንጀለኞችና የጁንታው ባላት የሀገር ሰላም ጠንቅ እንዳይሆኑ ከወዲሁ መሥራት እንደሚያስፈልግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛ የትግራይ ክልል ተወካይ ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ አስታወቁ።
ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በማይካድራም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ላይ በንፁሃን ላይ ጭፍጨፋ ፈፅመው ያመለጡ የሳምሪ ቡድኖችም ሆኑ ሌሎች የጁንታው አባላት ተጨማሪ የሰላም ጠንቅ ከመሆናቸው በፊት መንግሥትና ህዝቡ በመተባበር የጥፋት ኀይሉን በማደን ሊይዙና በህግ ተጠያቂ ሊያደርጉ ይገባል።
‹‹ለዚህም ከጎረቤት አገራት ጋር ያለንን ጥሩ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በመጠቀም በትብብር መሥራትና ጉዳዩንም መልክ ማስያዝ ይገባል›› ያሉት ወይዘሮ ያየሽ በተለይም የሀገሪቱን ሰላም ከማይሹ የውጭ ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው ችግር ከማስከተላቸው በፊት በከፍተኛ ጥንቃቄ መሠራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የህወሓት ጁንታ ያልዋለበትን ገድል ለትውልድ ሲሰብክ ኖሯል” ሜጀር ጄኔራል ሹማ አብደታ
Next articleበምስራቅ ጎጃም ዞን የእናርጂና እናውጋ ነዋሪዎች 2 ሚሊን ብር የሚጠጋ ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ ለአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ድጋፍ አደረጉ፡፡