የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ የባህርዳር ከተማ ኤርፖርት ስያሜ እንዲቀየር ወሰነ።

785
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ የባህርዳር ከተማ ኤርፖርት ስያሜ እንዲቀየር ወሰነ።
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) ባለፉት ዓመታት “የባህርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት ” ተብሎ ይጠራ የነበረው የባህርዳር አውሮፕላን ማርፊያ በህብረተሰቡ ፍላጎት ውይይት ሲደረግበት ቆይቶ በዛሬው ዕለት ታህሳስ 09/2013 የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ “የባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት” ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል ።
ይህ ስያሜ ከ1983 ዓ.ም በፊትም ይጠራበት እንደነበር ያስታወሰው የከንቲባ ኮሚቴው የህዝቡን ፍላግትና የከተማውን ወካይ ስያሜ በመምረጥ ስሙ እንዲቀየር በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።
ተቋርጦ የነበረውም የአውሮፕላን ትራንስፖርት ከነገ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ አገልግሎት እንደሚጀምር ነው አስተባባሪ ኮሚቴው የገለፀው። መረጃው የባህርዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበመቀሌ ከተማ ጁንታው ቀብሮት የነበረ የነዳጅ ታንከር ውስጥ ከ200 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ተገኘ፡፡
Next article“የህወሓት ጁንታ ያልዋለበትን ገድል ለትውልድ ሲሰብክ ኖሯል” ሜጀር ጄኔራል ሹማ አብደታ