
በመቀሌ ከተማ ጁንታው ቀብሮት የነበረ የነዳጅ ታንከር ውስጥ ከ200 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ተገኘ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) በመቀሌ ከተማ ልዩ ስሙ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጁንታው ለጦርነት ዓላማ ሊያውለው በድብቅ ቀብሮት የነበረ 13 የነዳጅ ታንከር ተገኝቷል።
በመከላከያ ሰራዊት የ25ኛ ፈንቅል ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ ምክትል ኦፕሬሽናል አዛዥ ሻምበል ዩሐንስ ማቲዎስ እንዳስታወቁት ጁንታው ለጦርነት ዓላማ አስቦ በድብቅ ቀብሮት የነበረው 13 የነዳጅ ታንከር በመከላከያ ሰራዊቱ አሰሳ በቁጥጥር ውሏል፡፡
በታንከሩም ከ200 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
ጁንታው የትግራይ ህዝብ በነዳጅ እጥረት እንዲቸገር በማድረግ ዘርፎ ለራሱ እኩይ አላማ ቀብሮት ቆይቷል ብለዋል።
ጁንታው የደበቀው ታንከር እንዲገኝ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ አስተዋፆ አድርጓል ነው ያሉት።
በአካባቢው ተቀብሮ ለነዳጅ ማጠራቀሚያ ሊውል የነበረ ተጨማሪ ዘጠኝ ታንከር መገኘቱንም ሻምበል ዮሐንስ አስታውቀዋል፡፡
የትህነግ ጁንታ ለራሱ ጥቅም ብቻ የቆመ የህዝብ ጠላት መሆኑን የሚያረጋግጡ የተለያዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች እየተገኙ ስለመሆኑም አብራርተዋል።
በመቀሌ በተደረገው አሰሳ ለህገ ወጥ ተግባር ሊውሉ የነበሩ ቁሳቁሶች መያዛቸውንም እንደተናገሩ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ