የትህነግ ቡድን የሕልውናው መሰረት በብሔረሰቦች መካከል ክፍፍልና ግጭት መፍጠር እንደነበር የሱማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለፁ፡፡

220
የትህነግ ቡድን የሕልውናው መሰረት በብሔረሰቦች መካከል ክፍፍልና ግጭት መፍጠር እንደነበር የሱማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለፁ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) የትህነግ ቡድን በተለያዩ ክልሎች ግጭት እንዲነሳ ሲያደርግ እንደነበር ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል፡፡
ቡድኑ በተለይ በአማራና ኦሮሞ መካከል ልዩነት እንዲኖር በዋናነት ሲሰራ እንደነበርም አቶ ሙስጠፌ ገልፀዋል፡፡
በሱማሌና በኦሮሞ ብሔረሰቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረው ግጭትም የዚህ የትህነግ ተግባር አካል እንጂ ብሔረሰቦቹ ለዘመናት አብረው በሰላም የኖሩ ናቸው ብለዋል ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡
ቡድኑ በሌሎች ክልሎች ግጭት እንዲባባስ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግና ትግራይ ክልል ውስጥ ግጭትን እንዲኖር የሚያደርግ አካል ባለመኖሩ ትግራይ ሰላማዊ ሆኖ እንዲታይ በማድረግ የ27 ዓመት የስልጣን ዘመኑ በሃገሪቱ ከመጣው ሪፎርም የተሻለ መሆኑን ለማሳየት ጥረት ሲያደርግ ነበር ብለዋል አቶ ሙስጠፌ፡፡
የትህነግ ቡድን ለ27 በዓመታት በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የፈጸመው ወንጀል ይቅርና በቅርቡ በማይካድራ የፈጸመው ወንጀል ብቻ እንደ ዓለም አቀፍ ሽብርተኛ እንዲፈረጅ ያደርገዋል ማለታቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየኢትዮ-ሩሲያ የጋራ ኮሚሽን የተሰሩ ሥራዎችን ገምግሟል፡፡
Next article“ከጁንታው ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለማተራመስ የሚሠሩ የውጭ ኃይሎችን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መታገል ይገባል” የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ