
የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ ኮሚሽን የተሰሩ ሥራዎችን ገምግሟል፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ኮሚሽን የኢኮኖሚ ፣ የሳይንስ ፣ የቴክኒክ እና የንግድ ትብብር ግምገማ በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡
በጋራ የኮሚሽኑ ግምገማ ላይ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ፣ የትምህርት ሚኒስትር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ(ዶ. ር) እና የሩሲያ ፌዴሬሽን የተፈጥሮ ሀብቶች እና የአካባቢ ጥበቃ ሚክትል ሚኒስትር እና የፌዴራል የማዕድን ሀብቶች ኤጀንሲ ኃላፊ ሚስተር ኤቭጂኒ ኪሴሌቭ ተሳትፈዋል፡፡
በውይይቱ በኮሚሽኑ 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ፕሮቶኮል ላይ የተላለፉ ውሳኔዎች አፈፃፀም ተገምግሟል ፡፡
ግብርና፣ ኢነርጂ ፣ ጂኦሎጂ፣ ትምህርት፣ ስፔስ ሳይንስን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የኢትዮጵያ ሩሲያ ትብብር ላይ ሀሳቦች ተለዋወጠዋል፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት እና በሩሲያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ በውይይቱ ተመላክቷል፡፡
የኮሚሽኑ 8ኛ መድረክ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ