በጎንደር ከተማ የጥምቀትን በዓል ሃይማኖታዊ ትውፊቱንና ባህሉን ጠብቆ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

270
በጎንደር ከተማ የጥምቀትን በዓል ሃይማኖታዊ ትውፊቱንና ባህሉን ጠብቆ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ትውፊቱንና ባህሉን ጠብቆ እንዲከበር በጎንደር ከተማ ከንቲባ የሚመራ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ ነው፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጂት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም የተመዘገበውን የጥምቀት በዓል በደመቀ መልኩ ለማክበር ከወዲሁ የጎንደር ከተማ ከንቲባ፣ የባህልና ቱሪዝም መምሪያ፣ የከተማዋ ሃገረስብከትና ነዋሪዎች በጋራ በመሆን እየሰሩ ነው፡፡
የከተማዋ ጽዳትና ውበት እንዲሁም የሆቴልና ቱሪዝም ስራዎቸም ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በዓሉ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በመሆኑ ትውፊቱን ሳይለቅ በዓሉን የሚያደምቁ የጎዳና ላይ ትርዒቶችና ባህሉን የሚገልፁ ስርዓቶቸ በከተማዋ ከያኒያን እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የቅርስ ባለሙያ አቶ ልዕልና ገብረመስቀል እንደነገሩን የመዋኛ ገንዳ ጥገናና እድሳት፣ የከተማ ጽዳትና ዉበት፣ የመብራት እድሳት ተሰርተዋል ብለዋል፡፡
በቀጣይ በጥምቀተ ባህሩ ከዚህ በፊት በእንጨት ተሰርተው አግልግሎት የሰጡ የእንጨት ርብራቦቸን ወደ ብረት ርብራብ ለመቀየር ምክክር እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- መሰረት ባየ- ከጎንደር
ቪዲዮ፡- በመላኩ ሙሉጌታ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleመንግሥት በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ቡድኖችን ለሕግ እንዲያቀርብ በአሜሪካ የኢትዮጵያን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚከታተል ድርጅት ጠየቀ፡፡
Next articleየአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የተሰነዘረበትን ጥቃት በመመከት ሕግ በማስከበር ዘመቻው ከፍተኛ ሚና እንደነበረው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ ማዕከል ሚኒስትር ዛዲግ አብርሃ አስታወቁ።