
የመጀመሪያው የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት አባላት ተመረጡ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) የገለልተኛ የብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ምስረታ የመንግሥትን የማሻሻያ ፕሮግራም በስኬት ለማስፈጸም ነው የተቋቋመው፡፡ ምክር ቤቱ የኢኮኖሚውን እድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ የምሁራንና የባለሙያዎችን ምክር እንዲሁም ግብረ መልስ ተግባራዊ ያደርጋል ነው የተባለው።
ገለልተኛ ከሆኑ ምሁራንና ባለሙያዎች ሃሳብ መቀበል የፖሊሲን አካታችነት ከመጨመር ባለፈ ያልታዩ ጉዳዮችን ለማየት፣ ሃገሪቱ ያለችበትን ውስብስብ የሆነ የድህነትንና ሌሎች ማኅበራዊ ችግሮችን ለመረዳትና ዉጤታማ የፖሊሲ አማራጮችን ለመመርመር ያስችላል ተብሏል።
ታህሳስ 21 ቀን 2012 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወጣው ማስታወቂያ መሰረት የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት እጩ አባላትን በጥቆማና በስራ ማመልከቻ መቀበል መጀመሩን ይፋ ሆኖ ነበር። ጥሪውን ተከትሎ በጥቅሉ ወደ 290 እጩዎች ቀርበዋል፡፡
በሦስት ደረጃ የተከፈለ የማጣራት ሂደት ከተከናወነ በኋላ ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ምሁራን ፍቃደኝነትታቸው ተረጋግጦ የመጀመሪያው የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት አባላት ሆነው እንዲመረጡ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።
በዚህም መሰረት
1.ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ
2. ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ
3. ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጀታ
4. ፕሮፌሰር መላኩ ደስታ
5. ፕሮፌሰር ሰይድ ሀሰን
6. ዶ/ር ታደለ ፈረደ
7. ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና
8 ዶ/ር አለማየሁ ስዩም
9.ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት
10. ዶ/ር ዲማ ነገዎ
11. ዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን
12. ፕሮፌሰር ለማ ወልደ ሰንበት
13. ዶ/ር ራሄል ካሳሁን
14. ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ
15. ዶ/ር ዮናስ ብሩ
16. አቶ ህላዊ ታደሰ ናቸው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ