መንግሥት በትግራይ ክልል የሚያከናውነውን የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ ቻይና እንደምትደግፍ የቻይና ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴንግ ሊ አስታወቁ።

248
መንግሥት በትግራይ ክልል የሚያከናውነውን የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ ቻይና እንደምትደግፍ የቻይና ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴንግ ሊ አስታወቁ።
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) በቻይና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከቻይና ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴንግ ሊ ጋር በወቅታዊ ሁኔታና በሁለቱ ሀገሮች የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይታቸው አምባሳደር ተሾመ በትግራይ ክልል የተካሄደውን ህግ የማስከበር ርምጃ በተመለከተ ቻይና ያሳየችውን የማይናወጥ አቋም አድንቀዋል።
በተባበሩት መንግስታት መድረክ ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን በመግለጽ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትን በመቃወምና “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ” በሚለው መርህ በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በኩል ለተሰየመው ከፍተኛ ልዑክ ላሳየችው ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት እና ምስጋና ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም በክልሉ የወታደራዊ ዘመቻው ተጠናቆ ወንጀለኞችን አድኖ የመያዝና ለህግ የማቅረብ ብሎም የመልሶ የመገንባት ስራ እየተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል።
የህዝቡን ሠላምና ደህንነት በማረጋገጥ እንዲሁም ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሰብዓዊ እርዳታ በማቅረብ ረገድ ተገቢው ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የቻይና ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ዴንግ ሊ ቻይና መንግስት የወሰደውን ህግ የማስከበር ርምጃ መደገፏን ገልፀዋል፡፡
ትግራይን መልሶ የመገንባትና በአፋጣኝ የክልሉን የመንግስት መዋቅር የመመሥረትና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እርዳታ ለማድረስ እየተደረገ ያለውን ጥረት የምትደግፍ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቻይና ስትራቴጂያዊ አጋር መሆኗን በመግለጽ ከሁለትዮሽ ግንኙነት በተጨማሪ በአለም አቀፍ መድረኮች በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ የሁለቱን ሃገራት ጥቅም በሚያስጠብቅ ሁኔታ አብረው መስራት እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየጎንደር ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ማሽን ያላቸው ባለሀብቶች ፈጥነው ወደሥራ እንዲገቡ ለማስቻል የተሟላ ሸድ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
Next article‹‹ ሠላሣ ሦስት ዓመት የበላንበቱ የጠጣንበቱ፤የታኅሣሥ ባታ ለት ተፈታ ወይ ቤቱ››