የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአዲስ አበባ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡

219

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአዲስ አበባ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 01/2013 ዓ.ም (አብመድ) የፅኑ ህክምና ከገቡት ውስጥ 59 በመቶ ህይታቸው አልፏል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መጥቷል፤ ለዚህም የማኅበረሰቡ መዘናጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።
በአዲስ አበባ በሐምሌ ወር ላይ ከነበረው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል የመጠቀም 78 በመቶ ምጣኔ አሁን ወደ 52 በመቶ መውረዱን አብራርተዋል።
አሁን በአዲስ አበባ ያለው የጽኑ ህሙማን ክፍል ማከሚያ ማእከላት መጨናነቃቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
የፅኑ ህክምና ክትትል ከገቡት ውስጥ 59 በመቶ ህይታቸው አልፏል።
በዚህም የፅኑ ህሙማን ክፍል የመጨረሻ የመቀበል አቅም ላይ እየደረሰ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡
ዶክተር ሊያ እንዳሉት ህብረተሰቡ የጥንቃቄ ትኩረቱን ካላጠናከረ ከባድ የህይወት መስዋትነት ሊያስከፍል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገኙት ክትባቶች በዚህ ዓመት ከሚያዝያ ወር በፊት እንደማይደርሱ ተናግረዋል።
መድሃኒቶቹ እንደተገኙ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለማቅረብ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን – ከአዲስ አበባ
Previous article“ጁንታው በእስር ቤት በሰለጠኑ ውሾች እስከማስነከስ ግፍ ፈጽሞብናል” የኮረም ከተማ ነዋሪዎች
Next article‹‹ አማርኛን በዓለም አቀፍ በተሸጠው እንግሊዘኛ ቋንቋ ደረጃ ማሰብ አለብን›› ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹ ሀሳብን በነጻነት መግለፅ ድንጋይ ከመወርወር ያድናል›› አርቲስት አስቴር በዳኔ