ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እድገት አስተዋፅኦ ያበረከቱ መሪዎች ተሸለሙ፡፡

226

ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እድገት አስተዋፅኦ ያበረከቱ መሪዎች ተሸለሙ፡፡

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 30/2013 ዓ.ም (አብመድ) መሪዎቹ ሽልማት የተበረከተላቸው የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ላስመዘገባቸው ውጤቶችና ለድርጅቱ እድገት ያላሰለሰ ድጋፍ በማድረጋቸው ነው፡፡
ሽልማቱን ካገኙት መካከል የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወርቅሰሙ ማሞ፣ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ንጉሱ ጥላሁን፣ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዮሐንስ ቧያለው እና የቀድሞው የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ስዩም መኮንን ናቸው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleሳምሪ የማይካድራዎቹ አካዙ !
Next articleከ80 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሃብት አስመዝጋቢዎች የመጀመሪያ ደረጃ እና ዳግም ምዝገባ ማከናወኑን የአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡