“እኩይ ተልዕኮ ተሸክሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው የህወሓት ቡድን ተወግዶ መከበሩ ቀኑን ልዩ ያደርገዋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

189

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 29/2013 ዓ.ም (አብመድ) የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ህዝቦችን በማናከስ እኩይ ተልዕኮ ተሸክሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው የህወሓት ቡድን ተወግዶ መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።

15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የሃገር አቀፍ ሲምፖዚየም መርሐግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ራሳቸውን ችለው በልዮ ውበት የሚፈሱ ወንዞች ናቸው፤ ይሕም ውበታቸው ሕብረ ብሔራዊነትን የያዘ የአንድነት መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል።

በዓሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውበት ማሳያ ነው ብለዋል።

የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ልዮ የሚያደርገው ደግሞ ህዝቦችን በማናከስ እኩይ ተልዕኮ ተሸክሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው የህወሓት ቡድን ተወግዶ መከበሩ እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው ይህንን እኩይ ሓይል ለማስወገድ ዋጋ ለከፈሉ የጸጥታ ሀይሎችና ዜጎችም ምስጋና አቅርበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አገር አቀፍ ሲምፖዚየም መርሐግብር እየተካሄደ ነው፡፡
Next articleበመተከል ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ እንዲቆም ከፌዴራል መንግስት ጋር በቅንጂት እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡