
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 29/2013 ዓ.ም (አብመድ) 15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አገር አቀፍ ሲምፖዚየም መርሐግብር በአዲስ አበባ በመካሔድ ላይ ይገኛል።
በመርሐግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮችና የብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች እና የሐይማኖት መሪዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
መርሐግብሩ በወራሪው፣ ተስፋፊውና አሸባሪው ትህነግ ቡድን ክህደት ተፈፅሞባቸው ለተሰው የሰራዊት አባላት የህሊና ጸሎት ተደርጎ ተጀምሯል።