“በትራንስፖርት ዘርፍ የካርቦን ልቀት በሚቀንስበት ሁኔታ የምጣኔ ሀብትና የፈጠራ ስራዎች ሊበረታቱ ይገባል” የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ

275
“በትራንስፖርት ዘርፍ የካርቦን ልቀት በሚቀንስበት ሁኔታ የምጣኔ ሀብትና የፈጠራ ስራዎች ሊበረታቱ ይገባል” የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 25/2013 ዓ.ም (አብመድ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን በመወከል በዓለም አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የአየር ብክለት ጉባኤ ላይ የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
የዚህ ዓለም አቀፍ መድረክ ዋና አላማ ከአምስት ዓመታት በፊት ይፋ ከተደረገው የፖሪስ ስምምነት አንስቶ በትራንስፖርት ዘርፉ እየጨመረ የመጣውን የካርቦን ልቀት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በቀጣይ ዓመታት ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊሰሩ የሚገቡ ተግባራትን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ነው፡፡
ሚኒስትሯ ‘’En Route to COP 26’’ በተሰኘው በበይነ መረብ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የአየር ብክለት ጉባኤ ላይ የካርቦን ልቀትን በመቀነስ የአየር ብክለትን በመቆጣጠር ረገድ የትራስፖርት ዘርፍ መጠቀም የሚችላቸውን አማራጭ ሀሳቦች በዝርዝር በመግለጽ ኢትዮጵያ የዚህ እንቅስቃሴ አካል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ባለፋት ዓመታት እያከናወነች ያለችውን ጥረቶችን ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡
ሚኒስትሯ በትራንስፖርት ዘርፍ የካርቦን ልቀት በሚቀንስበት ሁኔታ የምጣኔ ሀብትና የፈጠራ ስራዎች ሊበረታቱ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ በቅርቡ የፀደቀውን የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ይዘትና ተግባራዊነት ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የትራንስፖርት ዘርፉን እንቅስቃሴ በማሻሻል እንዲሁም የእግርና የብስክሌት ጉዞን በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅን በመቀነስ ለአየር ብክለት ምክንያት ባለመሆን ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በመድረኩ ላይም የዓለም ባንክ ምክትል ኘሬዝዳንት ማክታር ዲዮኘ ጨምሮ የዓለም አቀፍ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት መሪዎች ተገኝተዋል፡፡
መረጃው ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ ነው፡፡
Previous articleከመንግስት ጎን በመቆም ለከተማዋ ዘላቂ ሰላም እንደሚሰሩ የኮረም ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
Next articleበጎ ፈቃደኛ መምህራን ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ሀገር ወዳድነታቸውን በተግባር እያሳዩ ነው፡፡