
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስወነጨፈቻትን ˝ኢት አር ኤስ ኤስ 1˝ ሳታላይት በይፋ ከቻይና ተረከበች፡፡
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 23/ 2013ዓ.ም (አብመድ) ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይናው ታዩዋን ከተማ የሳተላይት ማስወንጨፊያ ማዕከል ወደ ህዋ ያስወነጨፈቻትን ˝ኢት አር ኤስ ኤስ 1˝ በይፋ ከቻይና ተረክባለች።
የሳተላይቷ ይፋዊ ርክክብ ቀደም ብሎ በሁለቱ ሀገራት የዘርፉ መስሪያ ቤቶች በኩል ለማከናወን ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም የኮሮና ቫይረስ በፈጠረው የጉዞ መስተጓጎል ምክንያት ሳይከናወን መቆየቱ ተጠቁሟል።
በዚህም በሁለቱ ወገን በተደረሰ ስምምነት በቻይና ኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ እንዲረከቡ በተወሰነው መሰረት በቻይና ስፔስ ቴክኖሎጂ አካዳሚ በተካሄደ ስነ-ስርዓት ርክክቡ መፈፀሙን ፋብኮ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ሳይተላይቷን ማስወንጨፏ የሚታወስ ነው።