
“ህወሃት በስሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ክህደት በኢትዮጵያ ብሔር ብሔርብሔረሰቦችና ህዝቦች ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው” የእዙ አባላት
ባሕር ዳር: ኅዳር 23/2013 (አብመድ) ዘራፊውና ከሃዲው የጁንታው ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስሜን እዝ አባላት ላይ ባደረሰው ጥቃት ታስረው የነበሩ የሰራዊት አባላት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ ገብተዋል፡፡
የሰራዊቱ አባላት ለአብመድ እንደተናገሩት የሃገር መከላከያ ሰራዊት ለትግራይ ህዝብ በጉ አድራጎት ስራዎችን በማከናወን ባለውለታ ነው፤ ብዙ ዋጋ ለከፈለ ሰራዊት የሚከፈለው ይህ አልነበረም ብለዋሌ፡፡
በሰራዊቱ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላም ከሳምንት በላይ ብዙ ስቃይ እና እንግልት ደርሶብናል፤ ጥቃቱም ኢ-ሰብአዊ እና ትውልድ የማይረሳው የክህደት ወንጀል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አምልጠው እስኪወጡ ድረስ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ታግተው ለርሃብና ለውሃ ጥም እንደተጋለጡም ገልጸዋል፡፡ ከታገቱበት በማምለጥ በበርሃ አቋርጠው በብዙ እንግልና ስቃይ አማራ ክልል እንደገቡም አስረድተዋል፡፡
ወደ ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳድር ስንገባም ህዝቡ ቤት ያፈራውን ምግብና ውሃ አቅርቦልናል፤ ለተደረገልን ግብዣና አቀባበልም ትልቅ አክብሮትና ምስጋና አለን ነው ያሉት፡፡
ዘጋቢ፡ ጸጋየ አይናለም – ከሰቆጣ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ