በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሸራሮ፣ ማይጸብሪና እና ማይካድራ በከፊል እንዲሁም በአላማጣ ሙሉ በሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

278
በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሸራሮ፣ ማይጸብሪና እና ማይካድራ በከፊል እንዲሁም በአላማጣ ሙሉ በሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 23/2013 ዓ.ም (አብመድ) ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌኮም አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
በአካባቢው በቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ላይ ያጋጠሙ ጉዳቶችን በመጠገንና መልሶ በማቋቋም እንዲሁም አማራጭ የሃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም የቴሌኮም አገልግሎት በከፊልና ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡ በዚህም መሰረት በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሸራሮ፣ ማይጸብሪና እና ማይካድራ በከፊል እንዲሁም በአላማጣ ሙሉ በሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡
በሌሎች አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር የተጎዱ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን በመጠገን፣ መልሶ በማቋቋም ብሎም መደበኛ የኃይል አቅርቦትን ለማግኘት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክቷል፡፡
በሁሉም አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡
Previous articleበህግ ማስከበር የህልውና ዘመቻ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን የተወጡ የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ሰራተኞች በጎንደር አቀባበል ተደረገላቸው፡፡
Next article“ህወሃት በስሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ክህደት በኢትዮጵያ ብሔር ብሔርብሔረሰቦችና ህዝቦች ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው” የእዙ አባላት