በጎንደር ከተማ የሽብር ጥቃት ሊፈፅም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

293

በጎንደር ከተማ የሽብር ጥቃት ሊፈፅም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር የሽብር ጥቃት ሊፈፅም የነበረ ግለሰብ ከነመሳሪያው በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ እንዳሉት የከተማዋ ፖሊስና የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ባደረጉት ክትትል በከተማዋ የሽብር ጥቃት ሊፈጽም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር በዋለበት ቤት በተደረገ ፍተሻ 35 ተቀጣጣይ መሳሪያዎች፣ 20 የባንክ ገቢ ያደረገባቸው ደረሰኞች፣ የባንክ ደብተሮች፣ 216 የማሰልጠኛ ሰነዶች ከአንድ ላፕቶፕ ጋር መገኘቱን ነው የተናገሩት፡፡
ግለሰቡ በከተማዋ ሽብር ለመፍጠር ሲንቀሳቀስ የነበረ እንደሆነም ነው ኃላፊው የተናገሩት፡፡
ፖሊስ በከተማዋ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ እየተደረገ በሚገኘው የተቀናጀ ቁጥጥር የጁንታው ኃይል አባላትን ጨምሮ በከተማዋ ጥቃት የሚያደርሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ ማኅበረሰብም ማንኛውንም አጣራጣሪ ነገር ሲያይ ለጸጥታ ኃይሉ ጥቆማ እንዲደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- እመቤት ሁነኘው – ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleየትህነግ ጁንታ ቡድን ግፍ እና ሸፍጥ በቀድሞ የሰሜን ጎንደር ዞን ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙለዓለም ገሌ አንደበት
Next articleበሩዋንዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ800 ሽህ ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ፡፡