የትህነግ ጁንታ ቡድን ግፍ እና ሸፍጥ በቀድሞ የሰሜን ጎንደር ዞን ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙለዓለም ገሌ አንደበት

479

የትህነግ ጁንታ ቡድን ግፍ እና ሸፍጥ በቀድሞ የሰሜን ጎንደር ዞን ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙለዓለም ገሌ አንደበት

ባሕር ዳር: ኅዳር 22/2013 (አብመድ) አባቶቻችን ደማቸውን አፍስስው እና አጥንታቸውን ከስክሰው ኢትዮጵያ የምትባል የብዙኃን እናት መስርተዋል፡፡ አንድነቷ፣ ክብሯ እና ማንነቷ ተጠብቆ በብርቱዎች እንኳን ያልተደፈረችን ሀገር ዕድሉን አግቶ ለ27 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆየው የትህነግ ጁንታ የራሱን ጥቅም ብቻ በማስቀደም ኢትዮጵያውያንን በአንድ ጥላ ስር ማሰባሰብ አልቻለም፡፡
የትህነግ ጁንታ በኢትዮጵያ የፈፀማቸው ሁለንተናዊ የመብት ጥሰቶች እጅግ ውስብስብ፣ ረቂቅ እና ታሪክ ይቅር የማይላቸው ናችው፡፡ አቶ ሙሉዓለም ገሌ ከ1980ዎች ዓ.ም ጀምሮ የሰሜን ጎንደር ዞን ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የመተማ ወረዳ አስተዳደሪ ሆነው ለብዙ ዓመታት ሰርተዋል፡፡ “የአማራውን መሬት አሳልፌ አልሰጥም” በማለታቸው ከጁውንታው አባል አንዱ ከሆኑት አባይ ፀሐዬ በተሰጠ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በቡድኑ ማጎሪያ ቤት ለአምስት ዓመታት ያለምንም ጥፋት ተሰቃይተዋል፡፡
በጁንታው ማጎሪያ ቤትም በዓለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ሰቆቃ እንደ ተፈፀመባቸው አቶ ሙሉዓለም ገሌ ተናግረዋል፤ እንደ አቶ ሙሉዓለም ገሌ ትዝብት በማጎሪያ ቤቶቹ ዜጎች ከዱር አውሬ ጋር ታስረዋል፤ በግርፋት የተላላጠ ጎን ማሳረፊያ እንኳን የላቸውም፤ ብዙዎች በጨለማ ቤቶቹ ተሰቃይተዋል፤ በድብደባ ብዛት ህይወታቸውን አጥተዋል፤ አካላቸው ጎሎአል፤ ለስነልቦና ችግርም ተዳርገዋል፡፡
አቶ ሙሉዓለም እንደተናገሩት የትህነግ ጁንታ ቡድን ሲመሰረት ይዞት የተነሳው አሳብ ለሀገር የአንድነት ነቀርሳ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ህገወጡ ቡድን መጀመሪያም “ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ስትማቀቅ የኖረች ሀገር ናት” ብሎ መነሳቱን እና በሃሰት ትርክት ቅኝ ገዢ የሚያደርገው ደግሞ የአማራውን ህዝብ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቶ ሙሉዓለም ማብራሪያ የትህነግ ጁንታ ዓላማውን ካሳካ በኋላ አብሮ ሲታገሉ የነበሩትን ገድሏቸዋል፡፡ ጁንታው የመጀመሪያ ዓላማው ትግራይን ከኢትዮጵያ ህዝቦች መነጠል ነበር የሚሉት አቶ ሙሉዓለም የዚህ ማስፈጸሚያ ደግሞ የውሽት ፌዴራሊዝምን አሰረጸ፤ ዜጎች ያልተሳተፉበትን ህገ መንግስትም አረቀቀ ብለዋል፡፡
በዚህም በሀይል የአማራ ዕርሰት የነበሩትን ወልቃይት እና ጠገዴን ወደ ራሱ በማካለል በሱዳን በኩል የሀገር ሉዓላዊነትን የሚጻረሩ ሥራዎችን ሲሰራ እንደነበር ተናግረል፡፡ በስልጣን ዘመኑ በከፋፍለህ ግዛው መርህ የምጣኔ ሀብታዊ የበላይነት ለመውሰድ ከመሰቦ ሲሚንቶ እስከ ሁመራ ጥጥ መዳመጫ ፋብሪካዎችን ብዙ ቢሊዮን የሀገሪቱን ሀብት በማፍሰስ በመገባት ሲዘርፍ ቆይቷል ብለዋል አቶ ሙሉዓለም፡፡
ወልቃይት ጠገዴን እና ሁመራን ከወሰደ በኋላ ይህንን የሚታገሉ ንጹሃን የወልቃይት አርሶ አደሮችን፣ ታዋቂ አርበኞችን፣ ጀግኖችን እና ምሁራንን አንድ በአንድ በመልቀም ሽራሮ በመውሰድ ገድሎአቸዋል፤ ሌሎቹ እንዲሰደዱ እና በማረሚያ ቤት እንዲሰቃዩም አድርጓል ብለዋል፡፡ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያዊነት የማይደራደር እና በእኩይ ተግባሩ እንደማይተባበር በተደጋጋሚ እምቢተኝነቱን ስለገለጸ ያለ እርፍት ግድያና ጥላቻ እንደተሰራበት አቶ ሙሉዓለም ተናግረዋል፡፡
በተለይም በ2008 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ለመያዘ የሸረቡት ሴራ የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦችን በማስተሳሰር አሁን የሚታየው ለውጥ እንዲመጣ ያደረገ ትልቅ ድል ነበር ነው ያሉት፡፡
በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመውን ክህደት ተከትሎ መንግስት በወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ የትግራይ ህዝብ ከጁንታው ጨቋኝ አገዛዝ ነፃ እንዲወጣ አድርጓም ብለዋል አቶ ሙሉዓለም፡፡ ፋሽስት የውጭ ወራሪ እኳን በወረረበት ዘመን መሰረተ ልማት ሲዘረጋ እንደነበር አስታውሰው፤ ወንበዴው ግን በህዝብ ገንዘብ የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን ማፈራረሱ ለህዝብ ደንታ እንደሌለው ያስመሰከረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ወንበዴውን ቡድን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ማክሰም፣ በአሸባሪነትም መፈረጅ፣ ከምርጫ ቦርድም መሰረዝ እና ሀገር እንደ ሀገር የምትቀጥልበትን መፍትሔ ማስቀመጥ የቀጣይ ተግባር መሆን እንዳለበት አቶ ሙሉዓለም አመላክተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ሰሜን ጎንደር ዞን ስንደርስ እንደ አዲስ የተወለድን ያክል ተሰምቶናል” ከሰሜን እዝ ታፍነዉ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት
Next articleበጎንደር ከተማ የሽብር ጥቃት ሊፈፅም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡