“ሰሜን ጎንደር ዞን ስንደርስ እንደ አዲስ የተወለድን ያክል ተሰምቶናል” ከሰሜን እዝ ታፍነዉ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት

797
“ሰሜን ጎንደር ዞን ስንደርስ እንደ አዲስ የተወለድን ያክል ተሰምቶናል” ከሰሜን እዝ ታፍነዉ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 22/2013 ዓ.ም (አብመድ)
ጁንታዉ የህዋሃት ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቅምት 24 ጥቃት ማድረሱ ይታወቃል ፤ ይህንን ተከትሎ በሰሜን እዝ የነበሩና በጁንታዉ ቡድን ታፍነዉ የነበሩ የሰራዊት አባላት በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር በየዳ ወረዳ እየገቡ ይገኛሉ፡፡
እስካሁን ባለዉ መረጃ ከ3 ሺህ በላይ የሰራዊት አባላት በተከዜ በኩል አድርገዉ ወደ አማራ ክልል መግባታቸዉን ከበየዳ ወረዳ አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በጁንታዉ ታፍነዉ ከነበሩት አባላት መካከል ሃምሳ አለቃ ደምሰን አህመድ እንደሚለዉ ጁንታዉ ቡድን አሰቃቂ ግፍ እንደፈጸመባቸዉና ጁንታዉ ቡድን ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ጥቅምት 23 የአርሶ አደሮችን ሰብል እየሰበሰቡ እንደነበር ተናግሯል፡፡
የጁንታዉ ቡድን በሰሜን እዝ የ23ኛ ክፍለጦር አባላትን ትጥቅ ለማስፈታት ሽማግሌዎችን ቢልክም መከላከያ ሰራዊቱ ከራስ በፊት ህዝብን የሚያስቀድም በመሆኑ ትጥቃቸዉን አንፈታም ማለታቸዉን ሃምሳ አለቃ ይገዙ ወዬሶ ገልጸል፡፡
ለጁንታዉ ቡድን እጅ አንሰጥም ያሉት ለ18 ቀናት በተንቤን መምህራን ኮሌጅ ዉስጥ አፈና እንደተደረገባቸውና ሴቶችና መኮንኖችን የት እንደወሰዷቸዉ እንደማይታወቅም ገልጸዋል፡፡
ምንም እንኳን የጁንታዉ ቡደን አሰቃቂ ግፍ ቢፈጽምባቸዉም ተከዜን ተሸግረዉ አማራ ክልል ከጠለምት፣ በየዳና ደባርቅ እስከሚደርሱ የተደረገላቸዉ አቀባል ኢትዮጵዊነትን ያገኙበት እንደሆነም የሰራዊት አባላቱ ገልጸዋል፡፡
ከጁንታው ቡድን አምልጠው በሰንሰለታማ ተራራዎችና በአስቸጋሪ መልክዓ ምደር ተጉዘው ሰሜን ጎንደር ሲደርሱ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ከፍተኛ አቀባበልና እገዛ እንዳደረገላቸዉም ገልጸዋል፡፡
በአማራ ህዝብ የተደረገልን አቀባበል የድሮ የአባቶቻችን ፍቅር፣ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ያየንበት በመሆኑ ይህንም በሄድንባቸዉ የኢትዮጵያ ክፍሎች ሁሉ እንመሰክራለን ብለዋል፡፡
የበየዳ ወረዳ ህዘብ በጁንታዉ ቡድን ታፍነዉ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ወረዳው መግባታቸውን ሲሰማ ከህጻን እስከ አዋቂ ከፍተኛ የሆነ ደስታ እንደተሰማዉና አርሶ አደሩ የደከሙትን በበቅሎ በመሸኘት መተባበሩን የወረዳዉ ምክትል አስተዳዳሪ ታገኝ ዉባየሁ ገልጸዋል።
ደባርቅ ዩንቨርስቲ ከአካባቢዉ ማህረሰብና ወጣቶች ጋር በመተባበር ለሰራዊት አባላቱ የተቻለዉን ሁሉ እያደረገ መሆኑንም የደባቅ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀጃዉ ደማሙ ገልጸዋል፡፡
በጁንታዉ ቡድን ታፍነዉ የነበሩ የሰራዊት አባላት ከጁንታዉ ጋር ባለመተባበር ለሃገራቸዉ ትልቅ መስዋእትነት መክፈላቸዉንም ዶክተር ጀጃዉ ደማሙ አብራርተዋል፡፡
ዘጋቢ: – ደስታ ካሳ- ደባርቅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበሁመራ ከተማ በአንድ ሆቴል በተደረገ ፍተሻ ለ2ኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ።
Next articleየትህነግ ጁንታ ቡድን ግፍ እና ሸፍጥ በቀድሞ የሰሜን ጎንደር ዞን ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙለዓለም ገሌ አንደበት