
“ህገወጡ ትህነግ በአማራ ክልል በርካታ ግጭት እዲፈጠር ሲሰራ ነበር፤ ለምሳሌ የጎንደር ህዝብ ከሁሉም ብሄር ጋር ተዋዶ፣ ተጋብቶና ተዋልዶ ነው የሚኖረው፤ ትህነግም የቅማንትና የጎንደር ህዝብ አንድ ቤተሰብ ሆኖ እያለ ሲያጋጭ ነበር” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
ባህር ዳር: ኅዳር 21/2013 (አብመድ) “ባለፉት 2 ዓመታት ተኩል ኦሮሚያ ውስጥ 37 ግጭቶች ነበሩ በርካታ አማራዎችና ሌሎች ብሄሮች ሙተዋል፤ ኦሮሞ ከማንነቱ ወጥቶ እዲጋጭ ተደርጓል፤ ኦሮሞን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ እየሰራ ለኦሮሞ ተቆርቋሪ ነኝ ይላል በሚዲያው እየቀረበ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ በአማራ ክልልም በተመሳሳይ በርካታ ግጭት እዲፈጠር ተድርጓል ለምሳሌ የጎንደር ህዝብ ከሁሉም ብሄር ጋር ተዋዶ፣ ተጋብቶና ተዋልዶ ነው የሚኖረው፤ የቅማንትና የጎንደር ህዝብ አንድ ቤተሰብ የሆኑ ህዝቦች እዲጋጮ ተደረገ እስፖንሰር አድራጊው ደግሞ ህገወጡ የጥፋት ሀይል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ትግራይ ክልል ብዙ ብሄሮች አሉ ግን ግጭት የለም ምክንያቱም እነሱ ትግራይ ላይ ሆነው ሌሎች አካባቢወች ላይ ግጭት እዲፈጠር ነው የሚያደርጉት፤ ክልሎች ከክልሎች እዲሁም ክልሎች ውስጥ ያሉ ህዝቦች በብሄር እዲጋጩ ሲያደርጉ ነበር፤ በዚህ ብቻ አላበቃም የሱዳን ደንበር ጠባቂወችን እኛ ነን የሀገሪቱ ወታደሮች አሁን የፈለጋቹሁትን ደንበር መውሰድ ትችላላቹ አሏቸው በዚህ ጊዜ የሱዳን ሀይሎች እኛ በህጋዊ መንገድ እጂ ዝምብለን መሬት አንወስድም ማለታቸውን መረጃ ሰጥተውናል ማለታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤት አባላት ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ