“እኔ እደተሾምኩ ሁሉም የስራ እንቅስቃሴ የቤቴ ቁልፍ ሳይቀር በህወሃት ደህንነት አካላት እጂ ነበር” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

427

“እኔ እደተሾምኩ ሁሉም የስራ እንቅስቃሴ የቤቴ ቁልፍ ሳይቀር በህወሃት ደህንነት አካላት እጂ ነበር” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ባህር ዳር: ኅዳር 21/2013 (አብመድ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እየሰጡነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሹመታቸው ወቅት ያገጠማቸውን ፈተና ለምክር ቤት አባላት አብራርተዋል “ሌላው ቀርቶ ግቢ ዘወር ብየ ልይ ስል አይሆንም የተለመደ አይደለም ይላሉ፤ ግቢው የታወቀ ክፍለ ከተማም ቀበሌ የለውም፤ የላስቲክ ቤት አለ ደሳሳ ጎጆም አለ፤ ግቢው ከህግ ውጭ በህገወጥ የብሄራዊ ደህንነት ወታደር ያለበት ነው፤ በጥቅሉ የገባሁበት ግቢ ዘመናዊ እስር ቤት እንደሆነ አወኩ” ነው ያሉት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው “በመጀመሪው 2 ወር የስልጣን ቆይታየ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለሁ ነው ለውጥ የሚለው ከህዝቡ የቀረበው፤ በዚህ ሁኔታ መቀጠል ስለማይቻል ከህዝቡ ጋር እንገናኝ በማለት ስራ ጀመርን፤ ቅድሚያ ወደ ሶማሌ ክልል ሄድን መጀመሪያ ወደ ሶማሌ ክልል ለመሄድ ስንዘጋጂ አልሸባብ ይገልሀል የሚል መልስ ተሰጠኝ እኛም ሄድን፤ ሁለተኛ ወደ ትግራይ ስሄድ የትግራይ ህዝብም ለውጥ ፈላጊ በመሆኑ ከፍተኛ ድጋፍ አደረገ በዚህ ጊዜ ጁንታው ደነገጠ፤ ከህዝብ ሊነጥለን ነው በማለት ወደ አንቦ ለመሄድ ስናስብ አይሆንም አንቦ ኦነግ ይገልሀል አሉ፤ ግን ስኬታማ ነበር ከዛ ወደ ባህርዳርና ጎንደር ለመሄድ ስናስብም አይሆንም አሉ ደረሰን መጣንማ” በማለት በህገወጡ ቡድን የውስጥ ኃይል ይገጥማቸው የነበረውን ውስብስብ ችግር አንስተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ (ዶ/ር) አህመድ አዳርጋቸው ፅጌ እዲፈቱ ሲጠየቅ የህገወጡ የደህንነት ኃይል በግልፅ እኛ ካልንህ ውጭ ማድረግ አትችልም ወደሚል ጭቅጭቅ ተሂዶ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀጥሎም የሚያጋጥመውን ፈተና ለማቆም የደህንነት አካሉን ወደ መለወጥ ስራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡ ይሁንጂ በወቅቱ የነበሩት የደህንነት ሹሞች ከሹመታቸው እደተነሱ የማይታወቅ ሀብት ሰርቀው ወደ መቀሌ ገቡ፤ ምን እደሰረቁ ምን ያህል እደሰረቁ እንኳ አይታወቅም ምክንያቱም ደህንነት ተቋሙ የቤተሰብ ማህበር ነበር ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበህገወጥ ቡድኖች ላይ ቀድሞ ህግ የማሰከበር ርምጃ ለመውሰድ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደነበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡
Next article“ህገወጡ ትህነግ በአማራ ክልል በርካታ ግጭት እዲፈጠር ሲሰራ ነበር፤ ለምሳሌ የጎንደር ህዝብ ከሁሉም ብሄር ጋር ተዋዶ፣ ተጋብቶና ተዋልዶ ነው የሚኖረው፤ ትህነግም የቅማንትና የጎንደር ህዝብ አንድ ቤተሰብ ሆኖ እያለ ሲያጋጭ ነበር” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)