
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር መንግሥት ለሰጠው በሳል አመራር ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራና ለአፋር ልዩ ኃይል እንዲሁም ለአማራ ሚሊሻ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 21/2013 ዓ.ም (አብመድ)
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሕግ ማስከበር እንቅስቃሴው አድናቆትና ድጋፋቸውንም ገልፀዋል።
የምክር ቤት አባላት ይህን ያሉትም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ባለበት ነው፡፡
ከለውጡ ማግሥት ጀምሮ ሕወሀትና ኦነግ ሸኔ ተቀናጅተው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሀገርን ለመከፋፈልና ሕዝብን ከሕዝብ በጥርጣሬ እንዲተያይ የሚያደርጉ የሽብር ድርጊቶች ሲፈጽሙ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡
ነገር ግን በኢትዮጵያውያን በሳል የአስተሳሰብ ልዕልና ሀገርን የማበጣበጥ እቅዳቸው አለመሳካቱን ተነሰግረዋል፡፡
በዚህ የተበሳጩት የሕወሓት ህገወጥ ቡድኖች የሀገር አለኝታ በሆነው የመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ በዓለም ታሪክ ተደርጎ የማይታወቅ አሳፋሪና ዘግናኝ ድርጊት መጸሙን አንስተዋል፡፡
በማይካድራ ንጹኃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግፍ የተሞላበት ብሔር ተኮር ጥቃትም አውግዘዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ ሕገወጥ ቡድኑ የሀገርን ሕልውና አደጋ ላይ ለመጣል ያቀደውን ሴራ ለማክሸፍ እየተከናወነ ያለውን ሕግ የማስከበር ዘመቻ አድንቀዋል፡፡
በተለይም የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት በቆራጥነት ሕግ በማስከበር ዘመቻው የነበረውን ተጋድሎ አንስተዋል፡፡
አንጸባራቂ ድል ማስገኘታቸውን በማንሳትም የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስታላልፈዋል፡፡
በቀጣይ ህውሀትና አጋሩ ኦነግ ሽኔ በሽብርተኝነት ቡድን ተፈርጀው ሊያደርሱት የሚችሉትን እኩይ ተግባር ቀድሞ መከላከል እዲቻልም ጠይቀዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ