
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ከቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ የጁንታው ቡድን ይህን ያህል ዝግጅት ሲያደርግ መንግስት የት ነበር? መንግስት መረጃ አልነበረውም ወይ?
የህገወጡ የህወሃት ቡድን ባለፉት ዓመታት በሃገሪቱ ህዝቦች ላይ ከልክ ያለፈ ግፍ ሲፈፅም ቆይቷል አሁንም መንግስት በጊዜው ርምጃ ባለመውሰዱ ንፁሃን ዜጎች ጭፍጨፋ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ መንግስት በወቅቱ ርምጃ ያልወሰደበት ምክንያት ምንድን ነው?
አንድ ቡድን ሽብርተኛ ተብሎ ለመፈረጅ የሚያስችሉ ድርጊቶችን የህውሃት ቡድን ፈፅሟል፤ መንግስት ይህን ቡድን ሽብርተኛ ብሎ ለመፈረጅ ያልቻለበት ምክንያት ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች እስካሁን ተነስተዋል፡፡