የኢትዮጵያ ቅርሶች አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ተመሰረተ፡፡

506

የኢትዮጵያ ቅርሶች አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ተመሰረተ፡፡

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ቅርሶች አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ መመስረቱን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ብሔራዊ ኮሚቴው ከልዩ ልዩ ዘርፎች የተውጣጡ ምሁራን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ተመራማሪዎች እና ታዋቂ ሰዎችን ያካተተ 19 አባላት አሉት ተብሏል፡፡
ብሔራዊ ኮሚቴ በተለያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ ወጥተው በባዕድ ሀገራት የሚገኙ ቅርሶችን በማጥናት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር በወዳጅነትና በመግባባት መንፈስ ቅርሶቹን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የማድረገግ ዓላማ ያነገበ ነው ተብሏል፡፡
እንዲሁም ቅርሶቹን በሰላማዊ መንገድ መመለስ ባይቻል ዓለም አቀፍ ህግን ማዕከል አድርጎ እንደሚሰራም ነው የተገለጸው።
በምስረታ ጉባዔው ላይ ተገኝተው መድረኩን የከፈቱት የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ኢትዮጵያ እንደ ምድረ ቀደምትነቷ የብዝኀ ባህልና ቅርስ ባለቤት ናት ብለዋል።
ሚንስትሯ አክለውም ቀደምት አባቶቻችን በጥበብ የተራቀቁባቸውን ብዙ ቁጥር ያላቸው የሀገራችን ቅርሶች፣ ስዕላት፣ ንዋየ ቅድሳት፣ መጻሕፍት፣ የወታደርና የሲቪል አልባሳት፣ የጦር መሳሪያዎችና ሌሎችም ቅርሶቻችን በስጦታ፣ በስርቆት እና በጦርነት ዝርፊያ ወደ ውጭ ሀገራት መውጣታቸውን ነው ያስታወሱት።
በተጨማሪም ዛሬ በይፋ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ቅርሶች አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መሆኑንና የኢትዮጵያን የቅርስ ሀብቶች ከያሉበት አጥንቶ እንዲያስመልስ ታላቅ ሀገራዊ አደራ የተጣለበት ብሔራዊ ኮሚቴ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ፋብኮ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ቅርሶች አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ የራሱ ጽህፈት ቤት የሚኖረው ሲሆን፥ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአማካሪዎች ቡድን ይኖረዋልም ተብሏል።
ስራውን በአጭር ጊዜ እና በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስራት ያመቸው ዘንድ የተለያዩ ተግባርና ኃላፊነት ያላቸው አምስት ንዑሳን ኮሚቴዎች በስሩ እንደሚያዋቅርም ይጠበቃል።
የብሔራዊ ኮሚቴ የብሔራዊ ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር፡-
ዶክተር ሂሩት ካሳው
ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው
መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ
ሊቀ ካህናት አባይነህ አበበ
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ
ዶክተር አባተ ጌታሁን
ኢንጅነር መላኩ እዘዘው
አርክቴክት ማህደር ገብረ መድህን
ረዳት ፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያ
ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን
ዶክተር ሙሉጌታ ፍሰሀ
አቶ ወርቅነህ አክሊሉ
አቶ ዮሀንስ ካሳ
ዶክተር ዮናስ በየነ
አምባሳደር መሀመድ ድሪር
ዶክተር አህመድ ሀሰን
አርቲስት ዳሳለኝ ኃይሉ ናቸው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የአምባገነን መሪዎች ባህሪና እጣ ፋንታ”
Next article“የልዩ ኃይሉና የሚሊሻ ተጋድሎ ከዛታ ተራሮች ስር ”