የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተገለፀ፡፡

299
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተገለፀ፡፡
ባህር ዳር: ኅዳር 16/2013 (አብመድ) የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተገለፀ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች ብራሰልስ ተገናኝተው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መክረዋል።
ኮሚሽነሩ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ የአውሮፓ ህብረት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት የለውም ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለህብረቱ ስትራቴጂያዊ አጋር ሃገር መሆንዋን የጠቀሱት፤ በህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ንፁሃን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጥበት መንገድ ለማመቻቸት በመንግሥት የተጀመረውን ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።
ኢብኮ እንደዘገበው ኢትዮጵያ የአለምአቀፍ የሰብዓዊ ህግ ተፈፃሚ ለማድረግ ነባራዊ ሁኔታውን በማጥናት የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ የሚደረግበትን አግባብ አቶ ደመቀ አስረድተዋል።
ንፁሃን ዜጎች ለከፋ ቀውስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ እና የሰብዓዊ ድጋፍ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት የጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበማይካድራ የተፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋ በማንነት ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ ወንጀል መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
Next article‹‹የአማራ ክልል መሪዎችና ባለሀብቶች ማሽን ከሌላ ክልል አስመጥቶ መሥራት ሊሰማን ይገባል›› ርእሰ መስተዳደር አገኘሁ ተሻገር