
“ሀገራት በሌሎች የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ያለመግባት መርህን ሊያከብሩ ይገባል” ጠቅላይ ሚሊስትር ዐቢይ አህመድ
ባህር ዳር: ኅዳር 16/2013 (አብመድ) ሀገራት በሌሎች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህን ሊያከብሩ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ረጅም የሀገረ መንግስት ታሪክ ያላት ሃገር መሆኗን በመጥቀስ ከመጀመሪያዎቹ የመንግስታቱ ድርጅት ማህበር አባል ሃገር እና አንደኛዋ መስራች መሆኗንም አውስተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም አፍሪካ ህብረት ጠንሳሽና መስራች መሆኗን አስታውሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለባለብዙ ወገን ትብብር እና ለዓለም አቀፍ ህግጋት መርሆዎችና ህጎች ላይ ጠንካራ የሆነ የማይናወጥ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላት ሃገር ስለመሆኗም አውስተዋል፡፡
እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሰላም ለማስከበር ከተሰማሩ ወገኖች መካከል በርካቶችን በቀዳሚነት ማበርከቷንም ጠቅሰዋል፡፡
ከተባበሩት መንግስታት ዋነኛ ህግጋት ውስጥ በአንቀጽ 2 (7) ላይ እንደሚደነግገው ማንኛውም ሃገር በአንድ ሉዓላዊ ሃገር ላይ ጣልቃ ስላለመግባት ይደነግጋል፡፡
የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤትም ይህንን ጉዳይ አጽንኦት በመስጠት አንድ ሉዓላዊ ሀገር የውስጥ ጉዳዩን ያለማንም ጣልቃ ገብነት የማካሄድ መብትን ያረጋግጣል፡፡ እነዚህ መርሆዎች ከአፍሪካ ህብረት ህግጋት ውስጥ የሚመነጩም ናቸው፡፡
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሁን መንግስት እያካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር ዘመቻ ለማገዝ ያሳየውን ፍላጎት ያደንቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ በዓለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት መከናወን እንዳለበት ለማስገንዘብ እንወዳለንም ብለዋል፡፡
ይህም የኢትዮጵያ መንግስት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥያቄዎችን እስከሚያቀርብ ድረስ ከጎኑ ሊቆሙ እንደሚገባ አጽንዖት ይሰጣል እንዳሉ ፋብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ