በደብረ ብርሀን ከተማ የቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት በማህበር የተደራጁ ከ700 በላይ ማህበራት መፍትሄ ሳያገኙ ዓመታት ተቆጥረዋል።

1164
በደብረ ብርሀን ከተማ የቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት በማህበር የተደራጁ ከ700 በላይ ማህበራት መፍትሄ ሳያገኙ ዓመታት ተቆጥረዋል።
ባህር ዳር: ኅዳር 15/2013 (አብመድ) በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ላለፋት ዓመታት በማህበር ተደራጅተው የቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት የሚጠባበቁ ዜጎች ቁጥር ከ16 ሺህ በላይ ደርሷል። እነዚህ ዜጎች የቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት ተደራጅተው ቢጠብቁም መፍትሄ ማግኘት አልቻሉም። አብመድ የደብረ ብርሀን ከተማን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ደስታ አንዳርጌን ጠይቋል። ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የቤት መስሪያ ቦታ ለማግኘት የሚጠባበቁ ዜጎች ያነሱት ቅሬታ ተገቢ መሆኑን አምነዋል።
እስካሁን ድረስ ለማህበራቱ እውቅና ወይም ህጋዊ ሰውነት አለመሰጠቱም ሌላው የቅሬታ ምንጭ ሆኗል። በከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት ጽሕፈት ቤት ምክትል ሀላፊ ሀይለማሪያም ንጉስ እስካሁን የ633 ማህበራት የመረጃ ማጣራት ስራው 80 በመቶ ተጠናቋል ብለዋል። ቅሬታ ላነሱት ማህበራት መቸ መልስ ይሰጣል ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ ምክትል ሀላፊው ቁርጥ ያለ መልስ መስጠት አልቻሉም።
የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ደስታ አንዳርጌ በበኩላቸው የማህበራቱ ጥያቄ ለመፍታት 785 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል ቢሉም ወደ ተግባር መቸ እንደሚገባ በትክክል አልገለጹም። ይህ የቦታ መጠን ሁሉንም ቅሬታዎች ማስተናገድ እንደማይቻልም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በደብረ ብርሃን ከተማ ለመኖያ ቤት መስሪያ ቦታ በመመሪያ የተቀመጠው የቦታ መጠን 200 ካሬ ቢሆንም ከተማ አስተዳደሩ በመመሪያው መሰረት እያስተናገደ አደለም። ሌላው በማህበራቱ የሚነሳው ቅሬታ የቁጠባና የክፍያ መጠን ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ በዚህ ጉዳይም ቁርጥ ያለ መልስ መስጠት አልቻለም።
ይሁን እንጅ የካሳ መጠኑ በመጨመሩ ምክንያት ካሁን በፊት ከነበረው ክፍያ ሊጨምር የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ካሁን በፊት በሄክታር እስከ 700 ሺህ ብር ሲከፈል የነበረ ሲሆን አሁን ባለው ስሌት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን እስከ 2 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ካሳ ክፍያ ሊተገበር እንደሚችል ተቀዳሚ ከንቲባው ለአብመድ ተናግረዋል።
በከተማዋ ዉስጥ የለውን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ጥያቄ ለመፍታት ዛሬም ማሰሪያ አልባ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል።
ዘጋቢ፡- ኤሊያስ ፈጠነ ፡ ከደብረ ብርሃን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአፋር ክልል የተለያዩ ዞኖችና ከተሞች ለሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ለአማራ ልዩ ኃይልና ለሚሊሻ አባላት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
Next article“ሀገራት በሌሎች የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ያለመግባት መርህን ሊያከብሩ ይገባል” ጠቅላይ ሚሊስትር ዐቢይ አህመድ