የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች የህወሓት ጽንፈኛው ቡድን አባላት መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅ እንዲሰጡ ጠየቁ፡፡

348
የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች የህወሓት ጽንፈኛው ቡድን አባላት መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅ እንዲሰጡ ጠየቁ፡፡
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 15/2013 ዓ.ም (አብመድ) ነዋሪዎቹ መንግስት የጀመረው ህግ የማስከበር ስራም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ከ22 አመት በላይ በሰቆጣ ከተማ የኖሩት የቀድሞው ኢህዴን ታጋይ እና በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ እየሰሩ የሚገኙት የጌታቸው ረዳ እህት ዋና ሳጅን ትዕግስት ረዳ የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን ከለውጡ ወዲህ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚፈጥራቸው የጸጥታ ችግሮች የሰው ህይወትና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
ቡድኑ የተንኮል ሴራውን በማስፋት ለሃገሪቱ ደጀን በሆነው የሃገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት ኢትዮጵያዊ ከሆነ ወገን የማይጠበቅና አሳፋሪ ተግባር መሆኑንም ነው የተናገሩት።
የጽንፈኛው የህወሓት ቡድን በመንግስት በተሰጠው 72 ስዓት ውስጥ እጁን ሰጥቶ የህዝቡን ህይወት መታደግም አለበት ብለዋል።
የትግራይ ተወላጅ የሆኑት አቶ ገብረእግዚአብሄር ሃብቴ እንደተናገሩት ህገወጡ ህወሃት የፈፀመው ወንጀል ህዝቡ እርስ በርስ እንዲጫረስና ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ለማድረግ ነው፤ይህ ግን አይሳካለትም፡፡ መንግስት በቡድኑ ላይ እየወሰደ ያለው ህግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ለትግራይ ህዝብ በችግር ጊዜ በደረሰ መከላከያ ሠራዊት ላይ ህገወጡ ህወሃት የፈጸመው ጥቃት የጁንታው ስብስብ መገለጫ እንጂ የትግራይን ህዝብ አይወክልምም ነው ያሉት፡፡
ዘጋቢ፡- ጸጋየ አይናለም – ከሰቆጣ

በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw

ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየኢትዮጵያ እና የቻይና ፕሬዝዳንቶች የሀገራቱን ፍሬያማ የጋራ ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
Next articleየአፋር ክልል የተለያዩ ዞኖችና ከተሞች ለሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ለአማራ ልዩ ኃይልና ለሚሊሻ አባላት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።