
የትህነግ ዘራፊ ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 15/2013 ዓ.ም (አብመድ) የትህነግ ዘራፊ ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ በተሽከርካሪ ተጭኖ ከሁመራ ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ሊገባ ሲል መያዙን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ቴዎድሮስ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮማንደር ዘለቀ ምትኩ ተናግረዋል፡፡ የተገኘው አደንዛዥ እፅ ካናቢስ የተሰኘ ነው፡፡
በዓለም አቀፍ ህግ የተከለከለውን እፅ የትህነግ ዘራፊ ቡድን እድሜያቸው ለጦርነት ያልደረሱ ህፃናት እንዲጠቀሙት በማድረግ ወደ ጦርነት እያስገባቸው መሆኑን እጃቸውን የሰጡ የትህነግ የልዩ ኃይል አባላት መናገራቸውን ዋና አዛዡ ገልጸዋል፡፡
ዘራፊ ቡድኑ ህፃናትን ወደ ጦርነት ማስገባቱ ሳያንስ ዓለም አቀፍ ወንጀል የሆነውን አደንዛዥ ዕፅ ህፃናት እንዲጠቀሙ ማድረጉ የወረደ ተግባር ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ከአደንዛዥ እፁ በተጨማሪ ህገወጡ ትህነግ በአልመዳ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ያመረታቸው የፌዴራል ፖሊስ ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የማረሚያ ቤት ፖሊስ አልባሳት አብሮ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮማንደር ዘለቀ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ሱራፌል ስንታየሁ
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m