አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የኢትዮ-ቻይና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሥረታ 50ኛ ዓመትን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የተላከ መልዕክት ለቻይና መንግስት አደረሱ፡፡

192
አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የኢትዮ-ቻይና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሥረታ 50ኛ ዓመትን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የተላከ መልዕክት ለቻይና መንግስት አደረሱ፡፡
ባህር ዳር: ኅዳር 14/2013 (አብመድ) በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የኢትዮጵያና የቻይና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሥረታ 50ኛ ዓመትን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ መንግስት የተላከ ‘የእንኳን አደረሰን’ መልዕክት አደረሱ።
መልዕክቱ የተላከው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለቻይና አቻቸው ፕሬዚዳንት ሺ ጂፕንግ እንዲሁም የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ መሆኑን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አመልክቷል።
‘የእንኳን አደረሰን’ የደስታ መግለጫ መልዕክቱን አምባሳደር ተሾመ በቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝተው ለአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ው ፔንግ ማድረሳቸውን ኤምባሲው ገልጿል።
ለቻይና አፍሪካ ግንኙነት ቀዳሚ ተምሳሌት እንደሆነ የሚነገርለት የኢትጵያና የቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበት 50ኛ አመት ክብረ በዓል በ2020 (እ.ኤ.አ) እየታሰበ ይገኛል።
ከአፍሪካ አገሮች ጋር በትብብር ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ቻይና ለኢትዮጵያ የገንዘብ፣ የሰው ሃይልና የቴክኒክ እንዲሁም የሌሎች መስኮች ድጋፍ እያደረገች ነው።
ባለፉት አመታትም የሁለቱ አገሮች መንግስትና ህዝቦች የተቀናጀ ጥረት በንግድና ኢንቨስትመንት የተሻለ ውጤት ሊያመጣ መቻሉ ይታወቃል።
የንግድ የኢንቨስትመንት ግንኙነቱ ወደፊት እየተጠናከረ የመጣ ሲሆን፤ የኢትዮጵያና ቻይና መልካም ግንኙት ቻይና በአፍሪካ ለምታደርጋቸው የትብብር መስኮች ተምሳሌት ተደርጎ ይቆጠራል።
በመሰረተ ልማት፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በኮንስትራክሽንና ሌሎችም የትብብር ስራዎች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራት ቻይና ዝግጁ መሆኗን ከዚህ ቀደም መግለጿ ይታወሳል።
ኢዜአ እንደዘገበው ሁለቱ አገሮች ባለፉት 50 አመታት በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ግንኙነቶችን መስርተዋል።
ቻይና በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በመላው አፍሪካ ከ43 አገሮች ሰፊ የልማትና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በማድረግ የአፍሪካ-ቻይናን ግንኙነቷን እያጠናከረች ትገኛለች።
በቅርቡ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ቻይና ለአፍሪካ ያደረገችውን ድጋፍ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አገሮች እንዲሰራጭ የላቀ ሚና መጫወቷ ይታወሳል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ያለመጠናቀቅና ለረጅም ጊዜ የመጓተት ችግር እየገጠማቸው ነው” የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
Next article“ልጆቻችን ሰኞ አስታጥቀው ማክሰኞ ለግዳጅ ዝመቱ አሏቸው፤ ዳሩ ግን በሰላም እጅ ሰጥተው ከእጃችን ገብተዋል”