“የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ያለመጠናቀቅና ለረጅም ጊዜ የመጓተት ችግር እየገጠማቸው ነው” የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

248
“የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ያለመጠናቀቅና ለረጅም ጊዜ የመጓተት ችግር እየገጠማቸው ነው” የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
ባህር ዳር: ኅዳር 14/2013 (አብመድ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ፣አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም በዛሬው ዕለት ገምግሟል።
ቋሚ ኮሚቴው በሃገሪቱ የተጀመሩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ያለመጠናቀቅና ለረጅም ጊዜ የመጓተት ችግር እንዳለ በግምገማው አንስቷል።
የመንገዶች ግንባታ የጥራት ችግርም ጎልቶ የሚታይ መሆኑን ያነሱት የቋሚ ኮሚቴው አባላት መንገዶች በተገነቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚፈራርሱ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኝ ለፕሮጀክቶቹ መጓተት የወሰን ማስከበር ፣ የካሳ ክፍያ መዘግየት እና የፀጥታ ችግሮች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ተቋራጮችን ገንብተው ከጨረሱ ከአንድ ዓመት በኋላ ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል አሰራር አለመኖሩ የጥራት ችግሩን ለመቅረፍ አስቸጋሪ እንዳደረገውም ኃላፊው ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ የመንገድ ግንባታውን የሚያጓትቱ ተቋማትን የማገድ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።
በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያሉ ፕሮጀክቶች የአካባቢ ጥበቃን መሰረት አድርገው እንዲገነቡና የአካባቢውን ነዋሪም ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ቋሚ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል።
ከመንገድ ግንባታዎች መጓተት እና ከጥራት ችግሮች ጋር በተያያዘ ቋሚ ኮሚቴው የሰጣቸው ግብረ መልሶች በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ትኩረት እንዲሰጣቸውም አባላቱ መጠየቃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article
Next articleአምባሳደር ተሾመ ቶጋ የኢትዮ-ቻይና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ምሥረታ 50ኛ ዓመትን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የተላከ መልዕክት ለቻይና መንግስት አደረሱ፡፡